Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ሰው በመንግሥትህ ውስጥ አለ፥ በአባትህም ዘመን እንደ አማልክት ጥበብ ያለ ጥበብና ማስተዋል እውቀትም ተገኘበት፥ አባትህ ንጉሡ ናቡከደነፆር የሕልም ተርጓሚዎችና የአስማተኞች የከለዳውያንና የቃላተኞች አለቃ አደረገው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በመንግሥትህ ውስጥ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት አንድ ሰው አለ፤ ይህ ሰው በአባትህ ዘመን እንደ አማልክት ጥበብና ማስተዋል፣ ዕውቀትም የሞላበት ሆኖ ተገኝቷል፤ አባትህ ንጉሥ ናቡከደነፆርም የጠንቋዮች፣ የአስማተኞች፣ የኮከብ ቈጣሪዎችና የመተተኞች አለቃ አደረገው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት አንድ ሰው በመንግሥትህ አለ፤ ይህ ሰው በአባትህ ዘመነ መንግሥት እንደ አማልክት የሆነ ዕውቀት፥ ጥበብና ማስተዋል የሞላበት ሆኖ ተገኝቶአል፤ በዚህም ምክንያት አባትህ ንጉሥ ናቡከደነፆር የጠንቋዮች፥ የአስማተኞች፥ የጠቢባንና የኮከብ ቈጣሪዎች ሁሉ አለቃ አድርጎ ሾሞት ነበር።

参见章节 复制




ዳንኤል 5:11
19 交叉引用  

ፈርዖንም ሎሌዎቹን እንዲህ አላቸው፦ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰው እናገኛለንን?


እኔም ባሪያህ፦ መልካሙንና ክፉውን ነገር ለመስማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኛል፥ አምላክህም እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን አልሁ።


እነሆ፥ ከዳንኤል ይልቅ ጥበበኛ ነህ፥ ምሥጢርም ሁሉ ከአንተ የተሸሸገ አይደለም።


በጥበብህና በማስተዋልህ ብልጥግናን ለራስህ አግኝተሃል ወርቅና ብርም በግምጃ ቤትህ ውስጥ ሰብስበሃል።


ንጉሡም የሚጠይቀው ነገር የቸገረ ነው፥ መኖሪያቸው ከሰው ጋር ካልሆነ ከአማልክት በቀር በንጉሡ ፊት የሚያሳየው ማንም የለም አሉ።


የጠለቀውንና የተሠወረውን ይገልጣል፥ በጨለማ ያለውን ያውቃል፥ ብርሃንም ከእርሱ ጋር ነው።


እኔ ንጉሡ ናቡከደነፆር ይህን ሕልም አልሜአለሁ፥ አንተም፥ ብልጣሶር፥ ፍቺውን አስታውቀኝ፥ የመንግሥቴ ጠቢባን ሁሉ ፍቺውን ያስታውቁኝ ዘንድ አይችሉምና፥ ነገር ግን የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ውስጥ አለና አንተ ትችላለህ።


ሕልም አለምሁ፥ እርስዋም አስፈራችኝ፥ በአልጋዬም ላይ የነበረው አሳቤና የራሴ ራእይ አስጨነቁኝ፥


ስለዚህ የሕልሙን ፍቺ እንዲያስታውቁኝ የባቢሎን ጠቢባን ሁሉ ወደ እኔ ይገቡ ዘንድ አዘዝሁ።


የአማልክት መንፈስ እንዳለብህ፥ እውቀትና ማስተዋልም መልካምም ጥበብ እንደ ተገኘብህ ስለ አንተ ሰምቻለሁ።


ንጉሡም አስማተኞቹንና ከለዳውያኑን ቃላተኞቹንም ያገቡ ዘንድ በታላቅ ድምፅ ጮኽ፥ ንጉሡም የባቢሎንን ጠቢባን፦ ይህን ጽሕፈት ያነበበ ፍቺውንም ያሳየኝ ሐምራዊ ግምጃ ይለብሳል፥ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዥ ይሆናል ብሎ ተናገረ።


ሕዝቡም፦ “የእግዚአብሔር ድምፅ ነው የሰውም አይደለም” ብለው ጮኹ።


ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሊቃኦንያ ቋንቋ፦ “አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል” አሉ፤


ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።


እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ፦ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።


跟着我们:

广告


广告