Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሕልም አለምሁ፥ እርስዋም አስፈራችኝ፥ በአልጋዬም ላይ የነበረው አሳቤና የራሴ ራእይ አስጨነቁኝ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አንድ ያስፈራኝ ሕልም አየሁ፤ በዐልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ፣ ወደ አእምሮዬ የመጡት ምስሎችና ራእዮች አስደነገጡኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዕለታት አንድ ቀን በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለ የሚያስፈራ ሕልምና የሚያስደነግጥ ራእይ አየሁ።

参见章节 复制




ዳንኤል 4:5
15 交叉引用  

ከሁለት ዓመት በኍላም ፈርዖን ሕልምን አየ፥ እነሆም በወንዙ ዳር ቆሞ ነበረ።


የጃንደረቦቹም አለቃ ስም አወጣላቸው፥ ዳንኤልን ብልጣሶር፥ አናንያንም ሲድራቅ፥ ሚሳኤልንም ሚሳቅ፥ አዛርያንም አብደናጎ ብሎ ጠራቸው።


ናቡከደነፆርም በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ናቡከደነፆር ሕልም አለመ፥ መንፈሱም ታወከ፥ እንቅልፉም ከእርሱ ራቀ።


ንጉሡም፦ ሕልም አልሜአለሁ፥ ሕልሙንም ለማወቅ መንፈሴ ታውኮአል አላቸው።


የራሴ ራእይ በአልጋዬ ላይ ይህ ነበረ፥ እነሆ፥ በምድር መካከል ዛፍ አየሁ፥ ቁመቱም እጅግ ረጅም ነበረ።


በአልጋዬም ላይ በራሴ ራእይ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ ቅዱስ ጠባቂ ከሰማይ ወረደ።


ነገር ግን ጉቶውን በምድር ውስጥ ተዉት፥ በመስክም ውስጥ በብረትና በናስ ማሰሪያ ታስሮ ይቈይ በሰማይም ጠል ይረስርስ እድል ፈንታውም በምድር ሣር ውስጥ ከአራዊት ጋር ይሁን።


የዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል አንድ ሰዓት ያህል አሰበ፥ ልቡም ታወከ። ንጉሡም መልሶ፦ ብልጣሶር ሆይ፥ ሕልሙና ፍቺው አያስቸግርህ አለው። ብልጣሶርም መልሶ አለ፦ ጌታዬ ሆይ፥ ሕልሙ ለሚጠሉህ፥ ፍቺውም ለጠላቶችህ ይሁን።


ንግሥቲቱም ስለ ንጉሡና ስለ መኳንንቱ ቃል ወደ ግብዣ ቤት ገባች፥ ንግሥቲቱም ተናገረች እንዲህም አለች፦ ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ፥ አሳብህ አያስቸግርህ፥ ፊትህም አይለወጥ።


የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ሰው በመንግሥትህ ውስጥ አለ፥ በአባትህም ዘመን እንደ አማልክት ጥበብ ያለ ጥበብና ማስተዋል እውቀትም ተገኘበት፥ አባትህ ንጉሡ ናቡከደነፆር የሕልም ተርጓሚዎችና የአስማተኞች የከለዳውያንና የቃላተኞች አለቃ አደረገው።


በባቢሎን ንጉሥ በብልጣሶር በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በአልጋው ላይ ሕልምንና የራሱን ራእይ አየ፥ ከዚያም በኋላ ሕልሙን ጻፈ፥ ዋነኛውንም ነገር ተናገረ።


የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው። እኔም ዳንኤል በአሳቤ እጅግ ተቸገርሁ፥ ፊቴም ተለወጠብኝ፥ ዳሩ ግን ነገሩን በልቤ ጠብቄአለሁ።


跟着我们:

广告


广告