Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 4:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እኔ ናቡከደነፆር በቤቴ ደስ ብሎኝ በአዳራሼም ተመችቶኝ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እኔ ናቡከደነፆር በቤቴ ደልቶኝ በቤተ መንግሥቴም ተመችቶኝ እኖር ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “እኔ ናቡከደነፆር በቤተ መንግሥቴ በብልጽግናና በምቾት እኖር ነበር።

参见章节 复制




ዳንኤል 4:4
13 交叉引用  

ኑ የወይን ጠጅ እንውሰድ፥ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፥ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፥ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል ይላሉ።


ሞዓብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ቅምጥል ነበረ፥ በአምቡላውም ላይ ዐርፎአል፥ ከዕቃውም ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፥ ወደ ምርኮም አልሄደም፥ ስለዚህ ቃናው በእርሱ ውስጥ ቀርቶአል፥ መዓዛውም አልተለወጠም።


በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፥ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፥ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ።


እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወንዞች መካከል የምትተኛና፦ ወንዙ የእኔ ነው ለራሴም ሠርቼዋለሁ የምትል ታላቅ አዞ፥ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ።


ንጉሡም የሚጠይቀው ነገር የቸገረ ነው፥ መኖሪያቸው ከሰው ጋር ካልሆነ ከአማልክት በቀር በንጉሡ ፊት የሚያሳየው ማንም የለም አሉ።


የዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል አንድ ሰዓት ያህል አሰበ፥ ልቡም ታወከ። ንጉሡም መልሶ፦ ብልጣሶር ሆይ፥ ሕልሙና ፍቺው አያስቸግርህ አለው። ብልጣሶርም መልሶ አለ፦ ጌታዬ ሆይ፥ ሕልሙ ለሚጠሉህ፥ ፍቺውም ለጠላቶችህ ይሁን።


የዚያን ጊዜም የንጉሡ ጠቢባን ሁሉ ገቡ፥ ነገር ግን ጽሕፈቱን ያነብቡ፥ ፍቺውንም ለንጉሡ ያስታወቁ ዘንድ አልቻሉም።


በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እመረምራለሁ፥ በአተላቸውም ላይ የሚቀመጡትን፥ በልባቸውም፦ እግዚአብሔር መልካምን አያደርግም፥ ክፉም አያደርግም የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።


跟着我们:

广告


广告