Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 4:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፥ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል፥ እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ፥ በሰማይም ጠል ትረሰርሳለህ፥ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከሕዝብ ተለይተህ ትሰደዳለህ፤ ዱር አራዊትም ጋራ ትኖራለህ። እንደ ከብት ሣር ትበላለህ፤ በሰማይ ጠልም ትረሰርሳለህ፤ ልዑሉ በሰዎች መንግሥታት ሁሉ ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለወደደው እንደሚሰጥ እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከሕዝብ መካከል ተለይተህ ትሰደዳለህ፤ ኑሮህም ከዱር አራዊት ጋር ይሆናል፤ ሰባት ዓመት እስኪያልፍ እንደ በሬ ሣር ትበላለህ፤ በሰማይ ጠል ትረሰርሳለህ፤ ይህም ሁሉ የሚደርስብህ ልዑል እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትንም ሁሉ ለወደደው ሰው እንደሚሰጥ እስከምትረዳ ድረስ ነው።

参见章节 复制




ዳንኤል 4:25
15 交叉引用  

ምድሪቱን በምድርም ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ ፈጥሬአለሁ፥ ለዓይኔም መልካም ለሆነው እሰጣታለሁ።


ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፥ ነገሥታትን ያፈልሳል፥ ነገሥታትንም ያስነሣል፥ ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል።


አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና ኃይልን፥ ብርታትንና ክብርን የሰጠህ የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ።


ንጉሡም ዳንኤልን፦ ይህን ምሥጢር ትገልጥ ዘንድ ተችሎሃልና በእውነት አምላካችሁ የአማልክት አምላክ፥ የነገሥታትም ጌታ፥ ምሥጢርም ገላጭ ነው ብሎ ተናገረው።


ልቡም ከሰው ልብ ይለወጥ፥ የአውሬም ልብ ይሰጠው፥ ሰባት ዘመናትም ይለፉበት።


ልዑሉ በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለወደደውም እንዲሰጠው፥ ከሰውም የተዋረደውን እንዲሾምበት ሕያዋን ያውቁ ዘንድ ይህ ነገር የጠባቂዎች ትእዛዝ፥ ይህም ፍርድ የቅዱሳን ቃል ነው።


ልዑል አምላክ በፊቴ ያደረገውን ተአምራቱንና ድንቁን አሳያችሁ ዘንድ ወድጃለሁ።


跟着我们:

广告


广告