Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 12:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሰማሁም ነገር ግን አላስተዋልሁም፥ የዚያን ጊዜም፦ ጌታዬ ሆይ፥ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድር ነው? አልሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እኔም ሰማሁ፤ ነገር ግን አላስተዋልሁትም፤ ስለዚህ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድን ነው?” ብዬ ጠየቅሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 መልአኩ የተናገረውን ሁሉ ሰማሁ፤ ነገር ግን ሊገባኝ አልቻለም፤ ስለዚህ “ጌታዬ ሆይ! የዚህ ሁሉ የመጨረሻው ውጤት ምን ይሆን?” ብዬ ጠየቅሁት።

参见章节 复制




ዳንኤል 12:8
9 交叉引用  

ራእዩም ገና ለብዙ ዘመን ነውና በኋለኛው ዘመን ለሕዝብህ የሚሆነውን አስታውቅህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ።


አንዱም ከወንዙ ውኃ በላይ የነበረውን በፍታም የለበሰውን፦ የዚህ ድንቅ ፍጻሜ እስከ መቼ ነው? አለው።


ከወንዙም ውኃ በላይ የነበረው በፍታም የለበሰው ሰው ቀኝና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፦ ለዘመንና ለዘመናት ለዘመንም እኵሌታ ነው፥ የተቀደሰውም ሕዝብ ኃይል መበተን በተጨረሰ ጊዜ ይህ ሁሉ ይፈጸማል ብሎ ለዘላለም ሕያው ሆኖ በሚኖረው ሲምል ሰማሁ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ዳንኤል ሆይ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ፥


ከቅዱሳኑም አንዱ ሲናገር ሰማሁ፥ ለተናገረው ለቅዱሱም ሁለተኛው ቅዱስ፦ ስለ ዘወትሩ መሥዋዕት፥ መቅደሱና ሠራዊቱም ይረገጡ ዘንድ ስለሚሰጥና ስለሚያጠፋ ኃጢአት የሆነው ራእይ እስከ መቼ ይሆናል? አለው።


እነርሱም ከዚህ ነገር ምንም አላስተዋሉም፥ ይህም ቃል ተሰውሮባቸው ነበር፥ የተናገረውንም አላወቁም።


ደቀ መዛሙርቱም ይህን ነገር በመጀመሪያ አላስተዋሉም፤ ነገር ግን ኢየሱስ ከከበረ በኋላ በዚያን ጊዜ ይህ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይህንም እንዳደረጉለት ትዝ አላቸው።


እርሱም፦ “አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤


በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።


跟着我们:

广告


广告