42 እጁን በአገሮች ላይ ይዘረጋል፥ የግብጽም ምድር አታመልጥም።
42 ሥልጣኑን በብዙ አገሮች ላይ ያንሰራፋል፤ ግብጽም አታመልጥም።
42 ሥልጣኑን በብዙ አገሮች ላይ በሚያንሰራፋበትም ጊዜ ግብጽም ራስዋ አታመልጥም።
የግብጽንም ምርኮ እመልሳለሁ፥ ወደ ተወለዱባትም ምድር ወደ ጳትሮስ እመልሳቸዋለሁ፥ በዚያም የተዋረደች መንግሥት ይሆናሉ።
ወደ መልካሚቱም ምድር ይገባል፥ ብዙ አገሮችም ይወድቃሉ፥ ነገር ግን ኤዶምያስና ሞዓብ ከአሞንም ልጆች የበለጡት ከእጁ ይድናሉ።
በወርቅና በብርም መዝገብ ላይ፥ በከበረችም በግብጽ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠለጥናል፥ የልብያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይከተሉታል።
ከምድርም ወገኖች ሁሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ለማይወጡ ለእነርሱ ዝናብ አይዘንብላቸውም።
በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።