Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 11:24 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በቀስታ ከአገር ሁሉ ወደ ለመለመችው ክፍል ይገባል፥ አባቶቹና የአባቶቹ አባቶች ያላደረጉትንም ያደርጋል፥ ብዝበዛውንና ምርኮውንም ሀብቱንም በመካከላቸው ይበትናል፥ በምሽጎችም ላይ እስከ ጊዜው ድረስ አሳቡን ይፈጥራል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የበለጸጉትን ክፍለ አገሮች በሰላም ሳሉ በድንገት ይወርራቸዋል፤ አባቶቹም ሆኑ አያቶቹ ያላደረጉትን ነገር ያደርጋል፤ ይከናወንለታልም፤ ብዝበዛውን፣ ምርኮውንና የተገኘውን ሀብት ሁሉ ለተከታዮቹ ያካፍላቸዋል፤ ምሽጎችን ለመጣል ያሤራል፤ ይህን የሚያደርገውም ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እጅግ ሀብታም የሆነ አንድ ክፍለ ሀገር በድንገት ይይዛል፤ ከቀድሞ አባቶቹ አንዱ እንኳ ያላደረገውን ነገር ሁሉ ያደርጋል፤ በጦርነት የማረከውንም ዕቃና ንብረት ሁሉ ለጭፍሮቹ ያከፋፍላል፤ በምሽጎች ላይ አደጋ ለመጣል ዕቅድ ያወጣል፤ ነገር ግን ለጥቂት ጊዜ ነው።

参见章节 复制




ዳንኤል 11:24
11 交叉引用  

ምሽጎቹንም ከተሞች የሰባውንም ምድር ወሰዱ፥ መልካሙን ነገር የሞሉትን ቤቶች፥ የተማሱትንም ጕድጓዶች፥ ወይኖቹንና ወይራዎቹን ብዙዎቹንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፥ በሉም፥ ጠገቡም፥ ወፈሩም፥ በታላቅ በጎነትህም ደስ አላቸው።


በመልካም ማሰማርያ አሰማራቸዋለሁ ጕረኖአቸውም በረጅሞቹ በእስራኤል ተራሮች ላይ ይሆናል፥ በዚያ በመልካም ጕረኖ ውስጥ ይመሰጋሉ፥ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ ማሰማርያ ይሰማራሉ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ነገር ወደ ልብህ ይገባል፥ ክፉ አሳብንም ታስባለህ፥


ከእርሱም ጋር ከተወዳጀ በኋላ በተንኰል ያደርጋል፥ ከጥቂትም ሕዝብ ጋር ወጥቶ ይበረታል።


በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፥ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።


ምድሪቱም ወፍራም ወይም ስስ፥ ዛፍ ያለባት ወይም የሌለባት እንደ ሆነች እዩ፤ ከምድሪቱ ፍሬ አምጡ፤ አይዞአችሁ። በዚያን ጊዜም ወይኑ አስቀድሞ ፍሬ የሚያፈራበት ወራት ነበረ።


ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?


ከበኣልብሪትም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፥ በዚያም አቤሜሌክ ምናምንቴዎችንና ወሮበሎችን ቀጠረበት፥ እነርሱም ተከተሉት።


跟着我们:

广告


广告