Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 11:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በእርሱም ስፍራ የተጠቃ ሰው ይነሣል የመንግሥቱንም ክብር አይሰጡትም፥ በቀስታ መጥቶ መንግሥቱን በማታለል ይገዛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “በርሱም ፈንታ የተናቀ ሰው ይነግሣል፤ ንጉሣዊ ክብርም አይሰጠውም፤ ሕዝቡ በሰላም ተቀምጦ ሳለ በተንኰል መንግሥቱን ይይዛል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ራእዩን ያብራራልኝ የነበረውም መልአክ እንዲህ አለ፦ “ከእርሱ በኋላ አንድ የተናቀ ሰው ይነሣል፤ የንጉሥነት ክብር ግን አልተሰጠውም፤ ነገር ግን በድንገት መጥቶ በተንኰል የመንግሥቱን ሥልጣን ይይዛል።

参见章节 复制




ዳንኤል 11:21
17 交叉引用  

ከእንግዲህ ወዲህ ሰነፍ ከበርቴ ተብሎ አይጠራም፥ ንፉግም ለጋስ አይባልም።


የዚያን ጊዜም በመንግሥቱ ክብር መካከል አስገባሪውን የሚያሳልፍ በስፍራው ይነሣል፥ ነገር ግን በቍጣው ሳይሆን በሰልፍም ሳይሆን በጥቂት ቀን ይሰበራል።


ቃል ኪዳኑን የሚበድሉትንም በማታለል ያስታል፥ ነገር ግን አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝብ ይበረታሉ፥ ያደርጋሉም።


በወደቁም ጊዜ በጥቂት እርዳታ ይረዳሉ፥ ብዙ ሰዎችም በግብዝነት ወደ እነርሱ ተባብረው ይሰበሰባሉ።


ነገር ግን ከሥርዋ ቍጥቋጥ አንዱ በስፍራው ይነሣል፥ ወደ ሠራዊቱም ይመጣል፥ ወደ ሰሜንም ንጉሥ አምባ ይገባል፥ በላያቸውም ያደርጋል፥ ያሸንፍማል።


ልዑሉ በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለወደደውም እንዲሰጠው፥ ከሰውም የተዋረደውን እንዲሾምበት ሕያዋን ያውቁ ዘንድ ይህ ነገር የጠባቂዎች ትእዛዝ፥ ይህም ፍርድ የቅዱሳን ቃል ነው።


ቀንዶችንም ተመለከትሁ፥ እነሆም፥ በመካከላቸው ሌላ ትንሽ ቀንድ ወጣ፥ በፊቱም ከቀደሙት ቀንዶች ሦስት ተነቃቀሉ፥ እነሆም፥ በዚያ ቀንድ እንደ ሰው ዓይኖች የነበሩ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበሩበት።


በመንግሥታቸውም መጨረሻ፥ ኃጢአታቸው በተሞላች ጊዜ፥ እንቈቅልሽን የሚያስተውል ፊተ ጨካኝ ንጉሥ ይነሣል።


በመታለሉ ተንኰልን በእጁ ያከናውናል፥ በልቡም ይታበያል፥ ታምነውም የሚኖሩትን ብዙዎችን ያጠፋል፥ በአለቆቹም አለቃ ላይ ይቋቋማል፥ ያለ እጅም ይሰበራል።


ከእነርሱም ከአንደኛው አንድ ታናሽ ቀንድ ወጣ፥ ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም ወደ መልካሚቱም ምድር እጅግ ከፍ አለ።


ልጆቹ የእርግማን ነገር እንዳደረጉ አውቆ አልከለከላቸውምና ስለ ኃጢአቱ በቤቱ ለዘላለም እንድፈርድ አስታውቄዋለሁ።


跟着我们:

广告


广告