Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 11:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በእርሱም ላይ የሚመጣው ግን እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፥ በፊቱም የሚቆም የለም፥ በመልካሚቱም ምድር ይቆማል፥ በእጁም ውስጥ ጥፋት ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ወራሪው ደስ ያሠኘውን ያደርጋል፤ ማንም ሊቋቋመው አይችልም። በመልካሚቱ ምድር ላይ ይገዛል፤ እርሷን ለማጥፋትም ኀይል ይኖረዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከወደ ሰሜን የሚመጣው ወራሪ የፈለገውን ያደርጋል፤ እርሱን ቆሞ የሚመክት አይኖርም፤ እርሱ የተቀደሰችውን አገር እንኳ ሳይቀር ወሮ ይይዛታል።

参见章节 复制




ዳንኤል 11:16
11 交叉引用  

እየጎረፈም ወደ ይሁዳ ይገባል፥ እያጥለቀለቀም ያልፋል፥ እስከ አንገትም ይደርሳል፥ አማኑኤል ሆይ፥ የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች።


እኔ ግን፦ ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አደርግሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር የከበረችውን የአሕዛብን ሠራዊት ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።


ኃያልም ንጉሥ ይነሣል፥ በትልቅ አገዛዝም ይገዛል፥ እንደ ፈቃዱም ያደርጋል።


ንጉሡም እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፥ ራሱንም ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ በአማልክት ሁሉ ላይ ራሱን ታላቅ ያደርጋል፥ በአማልክትም አምላክ ላይ በትዕቢት ይናገራል፥ ቍጣም እስኪፈጸም ድረስ ይከናወንለታል፥ የተወሰነው ይደረጋልና።


ወደ መልካሚቱም ምድር ይገባል፥ ብዙ አገሮችም ይወድቃሉ፥ ነገር ግን ኤዶምያስና ሞዓብ ከአሞንም ልጆች የበለጡት ከእጁ ይድናሉ።


ንጉሣዊ ድንኳኑንም በባሕርና በከበረው በቅዱስ ተራራ መካከል ይተክላል፥ ወደ ፍጻሜው ግን ይመጣል፥ ማንም አይረዳውም።


ስለ ሰጠው ታላቅነት ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ በፊቱ ይንቀጠቀጡና ይፈሩ ነበር፥ የፈቀደውን ይገድል፥ የፈቀደውንም በሕይወት ያኖር ነበር፥ የፈቀደውንም ያነሣ፥ የፈቀደውንም ያዋርድ ነበር።


አውራውም በግ ወደ ምዕራብ ወደ ሰሜንም ወደ ደቡብም በቀንዱ ሲጐሽም አየሁ፥ አራዊትም ሁሉ ይቋቋሙት ዘንድ አልቻሉም፥ ከእጁም የሚያድን አልነበረም፥ እንደ ፈቃዱም አደረገ፥ ራሱንም ታላቅ አደረገ።


ወደ አውራውም በግ ሲቀርብ አየሁት፥ እርሱም ተመረረበት፥ አውራውንም በግ መታ፥ ሁለቱንም ቀንዶች ሰበረ፥ አውራውም በግ ሊቋቋመው ኃይል አልነበረውም፥ እርሱም በምድር ላይ ጥሎ ረገጠው፥ አውራውንም በግ ከእጁ ያድነው ዘንድ የሚችል አልነበረም።


ከእነርሱም ከአንደኛው አንድ ታናሽ ቀንድ ወጣ፥ ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም ወደ መልካሚቱም ምድር እጅግ ከፍ አለ።


በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፥ ከሙሴ ጋር እንደሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ አልጥልህም፥ አልተውህም።


跟着我们:

广告


广告