Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 10:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሬን ዳሰሰኝ፥ የዚያን ጊዜም አፌን ከፍቼ ተናገርሁ በፊቴም ቆሞ የነበረውን፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከራእዩ የተነሣ ሕመሜ መጣብኝ፥ ኃይልም አጣሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያም የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤ እኔም አፌን ከፈትሁ፤ መናገርም ጀመርሁ፤ በፊቴ የነበረውንም እንዲህ አልሁት፤ “ጌታዬ ሆይ፤ ከራእዩ የተነሣ ተሠቃይቻለሁ፤ ኀይልም ዐጣሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህ በኋላ ሰውን የሚመስለው እጁን ዘርግቶ ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤ እኔም እንዲህ አልኩት፦ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ራእይ በጣም ስላሳመመኝ ሰውነቴ ዛለ።

参见章节 复制




ዳንኤል 10:16
29 交叉引用  

ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “ጌታ ሆይ! እኔ አፌ ኮልታፋ ምላሴም ጸያፍ የሆነ ሰው ነኝ፤ ትናንት ከትናንት ወዲያ ባሪያህንም ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይደለሁም።”


እርሱም፦ “ጌታ ሆይ! በምትልከው ሰው እጅ ትልክ ዘንድ እለምንሃለሁ፤” አለ።


በጥበብ መብዛት ትካዜ ይበዛልና፥ እውቀትንም የሚጨምር ኀዘንን ይጨምራልና።


አፌንም ዳሰሰበትና፦ እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፥ በደልህም ከአንተ ተወገደ፥ ኃጢአትህም ተሰረየልህ አለኝ።


እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ፥


በራሳቸውም በላይ ካለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበረ፥ በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ።


ነገር ግን በተናገርሁህ ጊዜ አፍህን እከፍታለሁ፥ እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና አንተ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሚሰማ ይስማ፥ የማይሰማም አይስማ ትላቸዋለህ።


ያመለጠውም ሳይመጣ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፥ አፌም ተከፈተች ከዚያም በኋላ እኔ ዲዳ አልሆንሁም።


ሰማሁም ነገር ግን አላስተዋልሁም፥ የዚያን ጊዜም፦ ጌታዬ ሆይ፥ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድር ነው? አልሁ።


የዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል አንድ ሰዓት ያህል አሰበ፥ ልቡም ታወከ። ንጉሡም መልሶ፦ ብልጣሶር ሆይ፥ ሕልሙና ፍቺው አያስቸግርህ አለው። ብልጣሶርም መልሶ አለ፦ ጌታዬ ሆይ፥ ሕልሙ ለሚጠሉህ፥ ፍቺውም ለጠላቶችህ ይሁን።


በእኔም በዳንኤል በሥጋዬ ውስጥ መንፈሴ ደነገጠች፥ የራሴም ራእይ አሰቸገረኝ።


የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው። እኔም ዳንኤል በአሳቤ እጅግ ተቸገርሁ፥ ፊቴም ተለወጠብኝ፥ ዳሩ ግን ነገሩን በልቤ ጠብቄአለሁ።


እኔም ዳንኤል ራእዩን ባየሁ ጊዜ ማስተዋሉን ፈለግሁ፥ እነሆም፥ የሰው ምስያ በፊቴ ቆሞ ነበር።


እኔም ወደ ቆምሁበት ቀረበ፥ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ፥ እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ራእዩ ለፍጻሜ ዘመን እንደ ሆነ አስተውል አለኝ።


ሲናገረኝም ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ፥ እርሱም ዳሰሰኝ ቀጥ አድርጎም አቆመኝ።


እኔም ዳንኤል ተኛሁ፥ አያሌም ቀን ታመምሁ፥ ከዚያም በኋላ ተነሥቼ የንጉሡን ሥራ እሠራ ነበር፥ ስለ ራእዩም አደንቅ ነበር፥ የሚያስተውለው ግን አልነበረም።


ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፥ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።


ያንጊዜም አፉ ተከፈተ መላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ።


ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።


ቶማስም፦ “ጌታዬ አምላኬም” ብሎ መለሰለት።


እርሱም፦ አይደለሁም፥ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው? አለው።


በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰው ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።


ማኑሄም፦ ጌታ ሆይ፥ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው፥ እባክህ፥ እንደ ገና ወደ እኛ ይምጣ፥ ለሚወለደውም ልጅ ምን እንድናደርግ ያስገንዝበን ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ።


ጌዴዎንም፦ ጌታዬ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? አባቶቻችንስ፦ እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ ተአምራቱ ወዴት አለ? ወዴት አለ? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፥ በምድያማውያንም እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል አለው።


እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ እስራኤልን በምን አድናለሁ? ወገኔ ከምናሴ ነገድ ከሁሉ ይልቅ የተጠቃ ነው፥ እኔም በአባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ አለው።


跟着我们:

广告


广告