Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ቈላስይስ 4:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ጌቶች ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና ለባሪያዎቻችሁ በጽድቅና በቅንነት አድርጉላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ጌቶች ሆይ፤ እናንተም በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ስለምታውቁ ባሮቻችሁን በፍትሕና በቅንነት አስተዳድሯቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌቶች ሆይ! እናንተ ደግሞ በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና ባርያዎቻችሁን በጽድቅና በቅንነት ተመልከቱአቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ጌቶች ሆይ! እናንተም በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ዐውቃችሁ አገልጋዮቻችሁን በቅንነትና በእኩልነት አስተዳድሩአቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ጌቶች ሆይ፥ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ችሁ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እው​ነ​ት​ንም ፍረዱ፤ በሰ​ማይ ጌታ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።

参见章节 复制




ቈላስይስ 4:1
22 交叉引用  

ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይመለከታልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በአገሩ ድሆች ሲገፉ፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ባየህ ጊዜ በዚህ ነገር አታድንቅ።


ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም? ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።


በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። የሞያተኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አይደርብህ።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፥ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እነዚያንም፦ እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ አላቸው። እነርሱም ሄዱ።


መንግሥትንም ይዞ በተመለሰ ጊዜ፥ ገንዘብ የሰጣቸውን እነዚህን ባሪያዎች ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ያውቅ ዘንድ እንዲጠሩለት አዘዘ።


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


እነሆ፥ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፥ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ፀባዖት ጆሮ ገብቶአል።


እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።


በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት፦ የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።


跟着我们:

广告


广告