Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 9:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ እህልም በወንፊት እንዲነፋ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እነፋለሁ፥ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “እነሆ፤ ትእዛዝ እሰጣለሁ፤ እህል በወንፊት እንደሚነፋ፣ የእስራኤልን ቤት፣ በሕዝብ ሁሉ መካከል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ እህልም በወንፊት እንደሚነፋ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “የእስራኤል ሕዝብ በሕዝቦች መካከል እንዲበተኑ አዛለሁ፤ የሚበተኑትም እህል በወንፊት እንደሚነፋ ዐይነት ነው፤ ነገር ግን ወንፊቱ ሲነቃነቅ ገለባው እንጂ አንድም ቅንጣት አይበተንም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እነሆ አዝ​ዛ​ለሁ፤ እህ​ልም በመ​ንሽ እን​ደ​ሚ​ዘራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል እዘ​ራ​ለሁ፤ ነገር ግን አን​ዲት ቅን​ጣት በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም።

参见章节 复制




አሞጽ 9:9
14 交叉引用  

በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።


የእንጀራ እህል ይደቅቃልን? ለዘላለም አያኬደውም፥ የሰረገላውን መንኮራኵርና ፈረሶቹን ምንም ቢያስኬድበት አያደቅቀውም።


እስትንፋሱም አሕዛብን በአጥፊ ወንፊት ሊነፋቸው እንደሚያጥለቀልቅ እስከ አንገትም እንደሚደርስ ወንዝ ነው፥ በሕዝብም መንጋጋ የሚያስት ልጓም ይሆናል።


ይህ ሕግ ከፊቴ ቢወገድ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያን ጊዜ ደግሞ የእስራኤል ዘር በፊቴ ሕዝብ እንዳይሆን ለዘላለም ይቀራል።


አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ አንተንም ያሰደድሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፥ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም።


ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፥ ወደ እነዚያም ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፥ ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች የማይደርሱበት ሕዝብ አይገኝም።


ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ። ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


ወደ አሕዛብም በተንኋቸው ወደ አገሮችም ተዘሩ፥ እንደ መንገዳቸውና እንደ ሥራቸው መጠን ፈረድሁባቸው።


እኔም ወደ አሕዛብ አስማርኬአቸዋለሁና፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም ሰብስቤአቸዋለሁና እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ በዚያም ከእነርሱ አንድ ሰው ከእንግዲህ ወዲያ አልተውም፥


ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፥ ፍርድንም አደርግብሻለሁ ከአንቺም የቀረውን ሁሉ ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ።


ከአንቺም ሢሶው በቸነፈር ይሞታል፥ በመካከልሽም በራብ ያልቃል፥ ሢሶውም በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል፥ ሢሶውንም ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ በኋላቸውም ሰይፍ እመዝዛለሁ።


እናንተም ከአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ።


ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤


እግዚአብሔርም ከምድር ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ወዳሉ አሕዛብ ሁሉ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተና አባቶችህ ያላወቃችኋቸውን ሌሎችን አማልክት፥ እንጨትንና ድንጋይን፥ ታመልካለህ።


跟着我们:

广告


广告