Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 8:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በውኑ ምድሪቱ ስለዚህ ነገር አትናወጥምን? በእርስዋም የሚኖር ሁሉ አያለቅስምን? ሙላዋም እንደ ወንዙ ትነሣለች፥ እንደ ግብጽም ወንዝ ትነሣለች ደግሞም ትወርዳለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “በዚህ ነገር ምድር አትናወጥምን? በውስጧ የሚኖሩትስ ሁሉ አያለቅሱምን? የምድር ሁለመና እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፤ እንደ ግብጽ ወንዝም ወደ ላይ ይፈናጠራል፤ ተመልሶም ይወርዳል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በውኑ ምድሪቱ ስለዚህ ነገር አትናወጥምን? በእርሷም የሚኖር ሁሉ አያለቅስምን? ሞላዋም እንደ ግብጽ ወንዝ አትነሳምን? እንደ ግብጽም ወንዝ ተናውጣም ዳግመኛ አትወርድምን?”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በዚህ ነገር ምድር ትናወጣለች፤ በአገሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የዓባይ ወንዝ ሞልቶ በመጒደል እንደሚናወጥ አገሪቱ በሞላ ትናወጣለች።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በውኑ ምድ​ሪቱ ስለ​ዚህ ነገር አት​ና​ወ​ጥ​ምን? በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖር ሁሉ አያ​ለ​ቅ​ስ​ምን? ጦር​ነት እንደ ወንዝ ይፈ​ስ​ሳል፤ እንደ ግብ​ፅም ወንዝ ይሞ​ላል፤ ደግ​ሞም ይወ​ር​ዳል።

参见章节 复制




አሞጽ 8:8
22 交叉引用  

ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነድዶአል እጁንም በላያቸው ዘርግቶ መትቶአቸዋል፥ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፥ ሬሳቸውም በአደባባይ መካከል እንደ ጕድፍ ሆኗል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።


ምድሪቱ የምታለቅሰው፥ የአገሩ ሣርስ ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቸ ነው? የተቀመጡባት ሰዎች፦ ፍጻሜያችንን አያይም ብለዋልና ስለ ክፋታቸው እንስሶችና ወፎች ጠፍተዋል።


ይህ እንደ ግብጽ ወንዝ የሚነሣ፥ ውኃውም እንደ ወንዝ የሚናወጥ ማን ነው?


ግብጽ እንደ ግብጽ ወንዝ ይነሳል ውኃውም እንደ ወንዙ ይናወጣል፥ እርሱም፦ እነሣለሁ ምድርንም ሁሉ እከድናለሁ፥ ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን አጠፋለሁ ብሎአል።


ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ያደርጋት ዘንድ የእግዚአብሔር አሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናውጣለች ታመመችም።


ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፥ የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፥ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፥ ጥፋትም ተቀጥሮአል።


የሰማርያ ሰዎች ስለ ቤትአዌን እምቦሳ ይፈራሉ፥ ክብሩም ከእርሱ ዘንድ ወጥቶአልና ሕዝቡ ያለቅሱለታል፥ የጣዖቱ ካህናትም በኀዘን ይንተባተባሉ።


ስለዚህ ምድሪቱ ታለቅሳለች፥ በእርስዋም የሚቀመጡ ሁሉ ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች ጋር ይደክማሉ፥ የባሕሩም ዓሦች ያልቃሉ።


ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬአችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፥ ማቅንም በወገብ ሁሉ፥ ራስ መንጨትንም በሁሉ ላይ አመጣለሁ፥ እንደ አንድያ ልጅም ልቅሶ፥ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድርን ይዳስሳል እርስዋም ትቀልጣለች፥ የሚኖሩባትም ሁሉ ያለቅሳሉ፥ ሙላዋም እንደ ግብጽ ወንዝ ትነሣለች፥ ደግሞም እንደ ግብጽ ወንዝ ትወርዳለች።


የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤


跟着我们:

广告


广告