Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 8:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ችጋረኛውን የምትውጡ፥ የአገሩንም ድሀ የምታጠፉ እናንተ ሆይ፦

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እናንተ ችግረኞችን የምትረግጡ፣ የምድሪቱንም ድኾች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ችግረኛውን የምትረግጡ፥ የአገሩንም ድሀ የምታጠፉ ይህን ስሙ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እናንተ የችግረኞችን መብት የምትረግጡና ድኾችን ከአገር ለማጥፋት የምትፈልጉ ሁሉ! ይህን ስሙ!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ችግ​ረ​ኛ​ውን በጥ​ዋት የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ድሃ የም​ት​ቀሙ እና​ንተ ሆይ!

参见章节 复制




አሞጽ 8:4
24 交叉引用  

ሚክያስም አለ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።


ድሆቹን ከመንገድ ያወጣሉ፥ የምድርም ችግረኞች ሁሉ ይሸሸጋሉ።


እናንተ የሰዶም አለቆች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ፥ የአምላካችንን ሕግ አድምጡ።


ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ ፌዘኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።


ነቢዩም ኤርምያስ ነቢዩን ሐናንያን፦ ሐናንያ ሆይ፥ ስማ፥ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል እንጂ እግዚአብሔር አልላከህም።


እናንተ ሰነፎች ልበ ቢሶች፥ ዓይን እያላችሁ የማታዩ፥ ጆሮም እያላችሁ የማትሰሙ ሕዝብ ሆይ፥ ይህን ስሙ።


በአንቺ ውስጥ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ከባልንጀሮችሽም በቅሚያ የስስትን ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እውነተኛ ሚዛን እውነተኛም የኢፍ መስፈሪያ እውነተኛውም የባዶስ መስፈሪያ ይሁንላችሁ።


ድሀውንም ደብድባችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፥ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም።


ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥ በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና።


አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፥ አንተ፦ በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፥ በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ ብለሃል፥


በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ በግዴታም ይይዙታል፥ በቤቶችም ላይ ይመኛሉ፥ ይወስዱአቸውማል፥ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ርስቱንም ይነጥቃሉ።


የሕዝቤን ሥጋ በልታችኋል፥ ቁርበታቸውንም ገፍፋችኋቸዋል፥ አጥንታቸውንም ሰብራችኋል፥ ለአፍላል እንደሚሆን ሥጋ ለድስትም እንደሚሆን ሙዳ ቈራረጣችኋቸው።


እኔም፦ ምንድር ናት? አልሁ። እርሱም፦ ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት አለኝ። ደግሞም፦ በምድር ሁሉ ላይ ያለ በደላቸው ይህ ነው አለ።


እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


ጻድቁን ኵኦንናችሁታል ገድላችሁትማል፤ እናንተን አይቃወምም።


跟着我们:

广告


广告