Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 6:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በመሰንቆም ድምፅ ለምትንጫጩ፥ እንደ ዳዊትም የዜማን ዕቃ ለምታዘጋጁ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ባልተቃኘ በገና እንደ ዳዊት ለምትዘፍኑ፣ በሙዚቃ መሣሪያ ለመጫወት ለምትሹ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በበገናም ድምፅ ለምትንጫጩ፥ እንደ ዳዊትም ለራሳችሁ የዜማን ዕቃ ለምታዘጋጁ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የሙዚቃ ቃና በመቃኘት በበገና የማይረባ ዘፈን ትዘፍናላችሁ፤ እንደ ዳዊትም ቅኔዎችን በማዘጋጀት በሙዚቃ መሣሪያ ታዜማላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ከበ​ገ​ናው ድምፅ ጋር አስ​ተ​ባ​ብ​ረው ለሚ​ያ​ጨ​በ​ጭቡ ሰዎች፤ ይኸ​ውም የማ​ያ​ልፍ ለሚ​መ​ስ​ላ​ቸ​ውና እን​ደ​ሚ​ያ​መ​ል​ጣ​ቸው ለማ​ያ​ውቁ፤

参见章节 复制




አሞጽ 6:5
12 交叉引用  

ስለምን በስውር ሸሸህ? ከእኔም ከድተህ ስለምን ኮበለልህ? በደስታና በዘፈም በከበሮና በበገና እንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም?


ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንድሞቻቸውን ይሾሙ ዘንድ ለሌዋውያን አለቆች ተናገረ።


አራቱ ሺህም በረኞች ነበሩ፤ አራቱ ሺህም ለምስጋና በተሰሩት በዜማ ዕቃዎች እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።


ሌዋውያንም የዳዊትን የዜማ ዕቃ ይዘው፥ ካህናቱም መለከቱን ይዘው ቆመው ነበር።


ብርንና ወርቅን የከበረውንም የነገሥታትና የአውራጆችን መዝገብ ሰበሰብሁ፥ አዝማሪዎችንና አርሆዎችን የሰዎች ልጆችንም ተድላ እጅግ የበዙ ሴቶችንም አከማቸሁ።


መሰንቆና በገና ከበሮና እምብልታም የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ፥ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፥ እጁም ያደረገችውን አላስተዋሉም።


የዘፋኞችሽንም ብዛት ዝም አሰኛለሁ፥ የመሰንቆሽም ድምፅ ከዚያ ወዲያ አይሰማም።


የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፥ የመሰንቆህንም ዜማ አላደምጥም።


የመቅደሱ ዝማሬ በዚያ ቀን ዋይታ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ የሰዎችም ሬሳ ይበዛል፥ በስፍራውም ሁሉ በዝምታ ይጣላል።


የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።


በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፥ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥


跟着我们:

广告


广告