Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ወይስ አንበሳ የሚነጥቀው ነገር ሳያገኝ በጫካ ውስጥ ያገሣልን? ወይስ የአንበሳ ደቦል አንዳች ሳይዝ በመደቡ ሆኖ ይጮኻልን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አንበሳ የሚበላውን ሳያገኝ፣ በጫካ ውስጥ ይጮኻልን? ምንም ነገርስ ሳይዝ፣ በዋሻው ውስጥ ያገሣልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ወይስ አንበሳ የሚነጥቀው ነገር ሳያገኝ በጫካ ውስጥ ያገሣልን? ወይስ የአንበሳ ደቦል አንዳች ነገር ሳይዝ በማደርያው ሆኖ ይጮኻልን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አንበሳ በደን ውስጥ ዐድኖ የሚበላውን ሳያገኝ በከንቱ ያገሣልን? የአንበሳ ደቦልስ አንዳች ነገር ዐድኖ ሳይዝ በሚኖርበት ቦታ ድምፁን ያሰማልን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ወይስ አን​በሳ የሚ​ነ​ጥ​ቀው ነገር ሳያ​ገኝ በጫ​ካው ውስጥ በከ​ንቱ ያገ​ሣ​ልን? ወይስ የአ​ን​በሳ ደቦል አን​ዳች ሳይዝ በመ​ደቡ ሆኖ በከ​ንቱ ይጮ​ኻ​ልን?

参见章节 复制




አሞጽ 3:4
7 交叉引用  

እግዚአብሔርን ይከተላሉ፥ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፥ ባገሣም ጊዜ ልጆች እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ።


እኔም ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፥ እኔም ነጥቄ እሄዳለሁ እወስድማለሁ፥ የሚያድንም አይገኝም።


እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፥ የእረኞችም ማሰማርያዎች ያለቅሳሉ፥ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።


በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን?


ወይስ ወፍ፥ አጥማጅ ከሌለው፥ በምድር ላይ በወጥመድ ይያዛልን? ወይስ ወስፈንጠር አንዳች ሳይዝ ከምድር ይፈነጠራልን?


አንበሳው አገሣ፥ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?


跟着我们:

广告


广告