Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 1:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በረባት ቅጥር ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ በሰልፍም ቀን በጩኸት በዐውሎ ነፋስም ቀን በሁከት አዳራሾችዋን ትበላለች፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በጦርነት ቀን በጩኸት ውስጥ፣ በማዕበል ቀን በዐውሎ ነፋስ ውስጥ፣ ምሽጎቿን እንዲበላ፣ በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በረባት ቅጥር ላይ እሳትን አነዳለሁ፤ በጦርነትም ቀን በጩኸት፥ በዐውሎ ነፋስም ቀን በሁከት የእርሷን የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ በራባ ከተማ ቅጽር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ ምሽጎችዋንም ያቃጥላል፤ ከዚህ በኋላ በጦርነቱ ቀን ጩኸትና ሁካታ ይበዛል፤ ጦርነቱም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይፈጥናል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በራባ ቅጥር ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በጦ​ር​ነት ቀን በጩ​ኸት መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋን ትበ​ላ​ለች፤ በፍ​ጻ​ሜ​ዋም ቀን ትና​ወ​ጣ​ለች።

参见章节 复制




አሞጽ 1:14
20 交叉引用  

እንዲህም ሆነ፥ በዓመቱ መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮአብን ከእርሱም ጋር ባሪያዎቹን እስራኤልንም ሁሉ ሰደደ። የአሞንም ልጆች አገር አጠፉ፥ ረባትንም ከበቡ፥ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።


ኢዮአብም የአሞንን ልጆች ከተማ ረባትን ወጋ፥ የውኃውንም ከተማ ያዘ።


በውስጥዋም የነበሩትን ሕዝብ አውጥቶ በመጋዝና በብረት መቆፈሪያና በብረት መጥረቢያ እንዲሠሩ አደረጋቸው፥ የሸክላ ጡብም እንዲያቃጥሉ አደረጋቸው፥ በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲህ አደረገ። ዳዊትም ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።


እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ ሠራዊቱን አወጣ፤ የአሞንንም ልጆች አገር አጠፋ፤ መጥቶም ረባትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ቈይቶ ነበር። ኢዮአብም ረባትን መትቶ አፈረሳት።


የመለከትም ድምፅ ሲሰማ፦ እሰይ! ይላል፥ ከሩቅ ሆኖ ሰልፍንና የአለቆቹን ጩኸት፥ የሠራዊቱንም ውካታ ያሸታል።


ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።


እግዚአብሔርም ክቡር ድምፁን ያሰማል፥ የክንዱንም መውረድ በሚነድድ ቍጣውና በምትበላ እሳት ነበልባል በዐውሎ ነፋስም በወጨፎም በበረዶ ጠጠርም ይገልጣል።


የሚረግጡ የሠልፈኞች ጫማ ሁሉ፥ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፥ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል።


እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፥ እርሱም ቍጣው፥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፍስ ወጥቶአል፥ የዓመፀኞችን ራስ ይገለባብጣል።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር።


ሰይፍ ወደ አሞን ልጆች አገር ወደ ረባት ወደ ይሁዳም ወደ ተመሸገች ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣ ዘንድ መንገድን አድርግ።


የቅጥሩን ማፍረሻ ያደርግ ዘንድ፥ አፍንም በጩኸት ይከፍት ዘንድ፥ በውካታም ድምፅን ከፍ ያደርግ ዘንድ፥ የቅጥሩን ማፍረሻ በበሮች ላይ ያደርግ ዘንድ፥ አፈርን ይደለድል ዘንድ፥ ምሽግም ይሠራ ዘንድ የኢየሩሳሌም ዕጣ በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ።


አንተም ቀንህ የደረሰብህ፥ የኃጢአትህ ቀጠሮ ጊዜ የደረሰብህ፥ ርኩስ ኃጢአተኛ የእስራኤል አለቃ ሆይ፥


የአሞንን ከተማ ለግመሎች ማሰማርያ፥ የአሞንንም ልጆች ለመንጋ መመሰጊያ አደርጋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ እጄን ዘርግቼብሃለህ፥ ለአሕዛብም አስበዘብዝሃለሁ፥ ከአሕዛብም ለይቼ እቈርጥሃለሁ፥ ከአገሮችም አጠፋሃለሁ እፈጅህማለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።


በፍጻሜ ዘመንም የደቡብ ንጉሥ ከእርሱ ጋር ይዋጋል፥ የሰሜንም ንጉሥ ከሰረገሎችና ከፈረሰኞች ከብዙም መርከቦች ጋር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣበታል፥ ወደ አገሮችም ይገባል፥ ይጐርፍማል፥ ያልፍማል።


በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የቂርዮትንም አዳራሾች ትበላለች፥ ሞዓብም በውካታና በጩኸት በመለከትም ድምፅ ይሞታል፥


ወደ ማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው። እንዲሁ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚተላለፍባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፥ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።


ከራፋይም ወገን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአሞን ልጆች አገር በረባት አለ፤ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።


跟着我们:

广告


广告