Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 8:27 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እርሱም ተነሥቶ ሄደ። እነሆ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ ባለሟልና የሀብት ንብረቷ ሁሉ አዛዥ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አገኘ። ይህም ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ሕንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሥልጣን የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ ኀላፊ አንድ ኢትዮጵያ ጃንደረባ ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እርሱም ተነሥቶ ሄደ፤ እነሆ፥ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ለእግዚአብሔር ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤ ይህ ሰው ሕንደኬ ለተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሟልና የገንዘብዋ ሁሉ ኀላፊ ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ሥት የሕ​ን​ደኬ ጃን​ደ​ረባ ከሹ​ሞ​ችዋ የበ​ለጠ፥ በሀ​ብ​ቷም ሁሉ ላይ በጅ​ሮ​ንድ የነ​በረ፥ አንድ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ሊሰ​ግድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 8:27
25 交叉引用  

የሳባም ንግሥት በእግዚአብሔር ስም የወጣለትን የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች።


በዚያን ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከረጅምና ከለስላሳ ሕዝብ፥ ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ከሆነ ወገን፥ ከሚሰፍርና ከሚረግጥ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ከሚከፍሉት ሕዝብ ዘንድ እጅ መንሻ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም ወደሚገኝበት ስፍራ ወደ ጽዮን ተራራ ይቀርባል።


ሰሜንን፦ መልሰህ አምጣ፥ ደቡብንም፦ አትከልክል፥ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፥ በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የግብፅ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፥ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፥ በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።


አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ።


የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፥ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፥ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ።


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ ወደ ፉጥ ወደ ሉድ ወደ ሞሳሕ ወደ ቶቤል ወደ ያዋን በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፥ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።


በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ።


በንጉሡም ቤት የነበረው ጃንደረባ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን በጕድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ። ንጉሡም በብንያም በር ተቀምጦ ነበር።


ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፥ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል።


ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ፥ የተበተኑትን ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል።


ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።


በበዓሉም ሊሰግዱ ከመጡት አንዳንዶቹ የግሪክ ሰዎች ነበሩ፤


ሲመለስም በሰረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር።


ሰምተን እናደርጋት ዘንድ ስለ እኛ ባሕሩን ተሻግሮ እርስዋን የሚያመጣልን ማን ነው? እንዳትል ከባሕሩ ማዶ አይደለችም።


አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ።


跟着我们:

广告


广告