Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 7:43 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ትሰግዱላቸውም ዘንድ የሠራችኋቸውን ምስሎች እነርሱንም የሞሎክን ድንኳንና ሬምፉም የሚሉትን የአምላካችሁን ኮከብ አነሣችሁ፤ እኔም ከባቢሎን ወዲያ እሰዳችኋለሁ’ ተብሎ እንዲህ ተጽፎአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ይልቁንም ልታመልኳቸው የሠራችኋቸውን፣ የሞሎክን ድንኳንና የኮከብ አምላክ የሆነውን የሬምፋም ጣዖት አንሥታችሁ ተሸከማችሁ። ስለዚህ ከባቢሎን ማዶ እንድትጋዙ አደርጋለሁ።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ትሰግዱላቸውም ዘንድ የሠራችኋቸውን ምስሎች እነርሱንም የሞሎክን ድንኳንና ሬምፉም የሚሉትን የአምላካችሁን ኮከብ አነሣችሁ፤ እኔም ከባቢሎን ወዲያ እሰዳችኋለሁ፤’ ተብሎ እንዲህ ተጽፎአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ይዛችሁ የሄዳችሁት የሞሎክን ድንኳንና ሬፋን የሚባለውን የአምላካችሁን ኮከብ ምስል ነበር፤ እነርሱም በእጃችሁ ሠርታችሁ ትሰግዱላቸው የነበሩ አማልክት ናቸው። እኔም ከባቢሎን ወዲያ እንድትሰደዱ አደርጋለሁ።’

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ነገር ግን የሞ​ሎ​ህን ድን​ኳን አነ​ሣ​ችሁ፤ ሬፋን የሚ​ባ​ለ​ው​ንም ኮከብ አመ​ለ​ካ​ችሁ፤ ትሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን አበ​ጃ​ችሁ፤ እኔም ወደ ባቢ​ሎን እን​ድ​ት​ማ​ረኩ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ።’

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 7:43
13 交叉引用  

በዚያን ጊዜም ሰሎሞን ለሞዓብ ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም ፊት ለፊት ባለው ተራራ ላይ መስገጃ ሠራ።


በሆሴዕ በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ወሰደ፤ እስራኤልንም ወደ አሦር አፈለሰ፤ በአላሔና በአቦር በጎዛንም ወንዝ በሜዶንም ከተሞች አኖራቸው።


የአሦር ንጉሥ እስራኤልን ወደ አሦር አፈለሰ፤ በአላሔና በአቦር በጎዛንም ወንዝ በሜዶንም ከተሞች አኖራቸው፤


ልጁንም በእሳት አሳለፈ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።


ይሁዳን ወደ ኃጢአት እንዲያገቡት፥ ይህንን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠሩ።


ከዘርህም ለሞሎክ በእሳት አሳልፈህ አትስጥ፥ የአምላክህንም ስም አታርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በውኑ በምድረ በዳ አርባ ዓመት ሙሉ መሥዋዕትንና ቍርባንን አቅርባችሁልኛልን?


跟着我们:

广告


广告