Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 7:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከመከራውም ሁሉ አወጣው፥ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖንም ፊት ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፥ በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይም ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከመከራው ሁሉ አወጣው፤ በግብጽም ንጉሥ በፈርዖን ፊት ሞገስና ጥበብን አጐናጸፈው፤ ፈርዖንም በግብጽና በቤተ መንግሥቱ ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ሾመው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከመከራውም ሁሉ አወጣው፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንም ፊት ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብጽና በቤቱ ሁሉ ላይም ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከመከራው ሁሉ አወጣው፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው። ንጉሡም በግብጽና በቤቱም ሁሉ ላይ አዛዥ አደረገው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከመ​ከ​ራ​ውም ሁሉ አዳ​ነው፤ በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊትም ሞገ​ስ​ንና ጥበ​ብን ሰጠው፤ በግ​ብ​ፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢት​ወ​ደድ አድ​ርጎ ሾመው።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 7:10
19 交叉引用  

እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ ምሕረትንም አበዛለት


ዮሴፍም በምድር ላይ ገዥ ነበረ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ ይሸጥ ነበር የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግምባራቸው ሰገዱለት።


ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ እንዲህም አለ፦ ጌታዬ ሆይ እኔ ባርያን በጌታዬ ጆሮ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ እኔንም ባሪያህን አትቆጣኝ አንተ እንደ ፈርዖን ነህና።


እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምን የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ በምድርም መካከል ይብዙ።


አንተንም የበደሉህን ሕዝብህን፥ በአንተም ላይ ያደረጉትን በደላቸውን ሁሉ ይቅር በል፤ ይራሩላቸውም ዘንድ በማረኩአቸው ፊት ምሕረት ስጣቸው፤


ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፤ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።


እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም፦ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።


跟着我们:

广告


广告