Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 27:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ልከኛም የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜ፥ እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሎአቸው ተነሡ በቀርጤስም አጠገብ ጥግ ጥጉን አለፉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 መጠነኛ የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜም እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሏቸው መልሕቁን ነቅለው፣ የቀርጤስን ዳርቻ በመያዝ ተጓዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ልከኛም የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜ፥ እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሎአቸው ተነሡ፤ በቀርጤስም አጠገብ ጥግ ጥጉን አለፉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አነስተኛ የደቡብ ነፋስ ሲነፍስ ባዩ ጊዜ እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሎአቸው መልሕቃቸውን አንሥተው ጒዞአቸውን ለመቀጠል ተነሡ፤ ከወደቡም ተነሥተው በቀርጤስ አጠገብ አድርገው ጥግ ጥጉን አለፉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ልከኛ የአ​ዜብ ነፋ​ስም ነፈሰ፤ እነ​ር​ሱም እንደ ወደዱ የሚ​ደ​ርሱ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር፤ መል​ሕ​ቁ​ንም አነሡ፤ በቀ​ር​ጤ​ስም አጠ​ገብ ሄዱ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 27:13
10 交叉引用  

በደቡብ ነፋስ ምድር ጸጥ ባለች ጊዜ፥ ልብስህ የሞቀች አንተ ሆይ፥


የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥ የደቡብም ነፋስ ና፥ በገነቴ ላይ ንፈስ፥ ሽቱውም ይፍሰስ፥ ውዴ ወደ ገነቱ ይግባ መልካሙንም ፍሬ ይብላ።


በአዜብም ነፋስ ሲነፍስ፦ ትኩሳት ይሆናል ትላላችሁ፥ ይሆንማል።


የቀርጤስና የዓረብ ሰዎች፥ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።”


ያም ወደብ ይከርሙበት ዘንድ የማይመች ስለ ሆነ፥ የሚበዙቱ ቢቻላቸው በሰሜንና በደቡብ ምዕራብ ትይዩ ወዳለው ፍንቄ ወደሚሉት ወደ ቀርጤስ ወደብ ደርሰው ይከርሙ ዘንድ ከዚያ እንዲነሡ መከሩ።


ሳይበሉም ብዙ ቀን ከቆዩ በኋላ፥ ያን ጊዜ ጳውሎስ በመካከላቸው ቆሞ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ሰዎች ሆይ፥ ሰምታችሁኝ በሆነ ኖሮ ከቀርጤስ እንዳትነሡ ይህንም ጥፋትና ጕዳት እንዳታገኙ ይገባችሁ ነበር።


በጭንቅም ጥግ ጥጉን አልፈን ለላሲያ ከተማ ወደ ቀረበች መልካም ወደብ ወደሚሉአት ስፍራ መጣን።


የገዛ ራሳቸው ነቢይ የሆነ ከእነርሱ አንዱ፦ የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው ብሎአል።


ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤


跟着我们:

广告


广告