Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 26:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እኔም፦ “ጌታ ሆይ፥ ማንነህ?” አልሁ። እርሱም አለኝ፦ “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፤ አንተ ማን ነህ?’ ” አልሁ። “ጌታም እንዲህ አለኝ፤ ‘እኔ፣ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እኔም ‘ጌታ ሆይ! ማን ነህ?’ አልሁ። እርሱም አለኝ ‘አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እኔም ‘ጌታ ሆይ! አንተ ማን ነህ?’ አልኩ፤ ጌታም እንዲህ አለኝ፦ ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እኔም፦ ‘አቤቱ አንተ ማነህ?’ አልሁ፤ ጌታም አለኝ፦ ‘እኔ አንተ የም​ታ​ሳ​ድ​ደኝ ኢየ​ሱስ ነኝ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 26:15
6 交叉引用  

ሙሴም፦ እግዚአብሔር ያንጎራጎራችሁበትን ማንጎራጎራችሁን ሰምቶአልና በመሸ ጊዜ ትበሉ ዘንድ ሥጋን፥ ማልዶም ትጠግቡ ዘንድ እንጀራን እግዚአብሔር ይሰጣችኋል፤ እኛም ምንድር ነን? ማንጎራጎራችሁ በእግዚአብሔር ላይ ነው እንጂ በእኛ አይደለም አለ።


ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።


ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።


ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ፦ “ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል” የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ።


ነገር ግን ተነሣና በእግርህ ቁም፤ ስለዚህ እኔን ባየህበት ነገር ለአንተም በምታይበት ነገር አገልጋይና ምስክር ትሆን ዘንድ ልሾምህ ታይቼልሃለሁና።


跟着我们:

广告


广告