Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 17:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነዚህም ሁሉ፦ ኢየሱስ የሚሉት ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ የቄሣርን ትእዛዝ ይቃወማሉ ብለው ጮኹ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ኢያሶንም በቤቱ ተቀብሏቸዋል፤ እነዚህም ሁሉ፣ ‘ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ’ በማለት የቄሳርን ሕግ የሚጥሱ ናቸው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነዚህም ሁሉ ‘ኢየሱስ የሚሉት ሌላ ንጉሥ አለ፤’ እያሉ የቄሣርን ትእዛዝ ይቃወማሉ፤” ብለው ጮኹ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ኢያሶንም ተቀብሎአቸዋል፤ ‘ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ’ እያሉም የሮምን ንጉሠ ነገሥት ትእዛዝ ይቃወማሉ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ይህ ኢያ​ሶ​ንም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በቄ​ሣር ላይ የወ​ን​ጀል ሥራ ይሠ​ራሉ፤ ሌላ ሕግ​ንም ያስ​ተ​ም​ራሉ፤ ኢየ​ሱ​ስም ሌላ ንጉሥ ነው” ይላሉ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 17:7
12 交叉引用  

በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፥ ንጉሥ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፥ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም።


የዚያን ጊዜም በንጉሡ ፊት መልሰው፦ ንጉሥ ሆይ፥ ከይሁዳ ምርኮኞች የሆነው ዳንኤል በየዕለቱ ሦስት ጊዜ ልመናውን ይለምናል እንጂ አንተንና የጻፍኸውን ትእዛዝ አይቀበልም አሉት።


ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው።


ይህ ሕዝባችንን ሲያጣምም ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል ደግሞም፦ እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ ሲል አገኘነው ብለው ይከሱት ጀመር።


ከዚህ በኋላ ጲላጦስ ሊፈታው ፈለገ፤ ነገር ግን አይሁድ፦ “ይህንስ ብትፈታው የቄሣር ወዳጅ አይደለህም፤ ራሱን ንጉሥ የሚያደርግ ሁሉ የቄሣር ተቃዋሚ ነው” እያሉ ጮኹ።


እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ” አሉ።


አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፥ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤


ሕዝቡና የከተማውም አለቆች ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ ታወኩ፥


እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?


በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤


跟着我们:

广告


广告