ሐዋርያት ሥራ 12:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ያወጣው ዘንድ አስቦ እያንዳንዱ አራት ወታደሮች ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ጴጥሮስን ወህኒ ቤት ካስገባው በኋላ፣ አራት አራት ወታደሮች እየሆኑ እንዲጠብቁት በአራት ፈረቃ ለተመደቡ ወታደሮች አስረከበው፤ ይህን ያደረገውም የፋሲካ በዓል ካለፈ በኋላ ሕዝብ ፊት አውጥቶ ሊያስፈርድበት ዐስቦ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው፤ ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ያወጣው ዘንድ አስቦ እያንዳንዱ አራት ወታደሮች ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ጴጥሮስን ካስያዘ በኋላ ወደ ወህኒ ቤት አስገባው፤ ከአይሁድ የፋሲካ በዓል በኋላ ለሕዝቡ እስኪያቀርበው ድረስ አራት አራት ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍሮች አስረከበው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ይዞም ወኅኒ ቤት አስገባው፤ ለሚጠብቁት ለዐሥራ ስድስቱ ወታደሮችም አሳልፎ ሰጠው፤ ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ሊያቀርበው ወድዶ ነበር። 参见章节 |