Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 12:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በተቀጠረ ቀንም ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋን ተቀመጠ እነርሱንም ተናገራቸው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በቀጠሮውም ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ለሕዝቡም ንግግር አደረገ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በተቀጠረ ቀንም ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋን ተቀመጠ፤ እነርሱንም ተናገራቸው፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በተቀጠረው ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለበሰና በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ለሕዝቡ ንግግር አደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን ሄሮ​ድስ ልብሰ መን​ግ​ሥ​ቱን ለብሶ፥ በአ​ደ​ባ​ባይ ተገ​ኝቶ ይፈ​ርድ ጀመረ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 12:21
10 交叉引用  

የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ልብሰ መንግሥት ለብሰው በሰማርያ በር መግቢያ አጠገብ በአደባባይ በዙፋኖቻቸው ላይ ተቀምጠው ነበር፤ ነቢያቶቹም ሁሉ በፊታቸው ትንቢት ይናገሩ ነበር።


የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ነው፥ በደኅንነቱም ሳለ ቀማኛ ይመጣበታል።


ሲዖልም ሆድዋን አስፍታለች፥ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፥ ከበርቴዎቻቸውና አዛውንቶቻቸው ባለጠጎቻቸውም ደስተኞቻቸውም ወደ እርስዋ ይወርዳሉ።


አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን፥ ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም ብላችኋል።


እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ ብላ ላከችበት።


ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎችም ጋር ተጣልቶ ነበር፤ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ መጡ፥ የንጉሥንም ቢትወደድ ብላስጦስን እሺ አሰኝተው ዕርቅ ለመኑ፥ አገራቸው ከንጉሥ አገር ምግብ ያገኝ ነበረና።


ሕዝቡም፦ “የእግዚአብሔር ድምፅ ነው የሰውም አይደለም” ብለው ጮኹ።


ከአምስት ቀንም በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚሉት ከአንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ እነርሱም ስለ ጳውሎስ ለአገረ ገዡ አመለከቱት።


በነገውም አግሪጳና በርኒቄ በብዙ ግርማ መጥተው ከሻለቆችና ከከተማው ታላላቆች ጋር ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስጦስም ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስን አመጡት።


跟着我们:

广告


广告