Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 12:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እነርሱም፦ “አብደሻል” አሉአት። እርስዋ ግን እንዲሁ እንደ ሆነ ታስረግጥ ነበር። እነርሱም፦ “መልአኩ ነው” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሰዎቹም፣ “አብደሻል እንዴ!” አሏት፤ እርሷ ግን ይህንኑ ደጋግማ በነገረቻቸው ጊዜ፣ “እንግዲያውስ የርሱ መልአክ ነው” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እነርሱም “አብደሻል!” አሏት። እርሷ ግን እንዲሁ እንደሆነ ታስረግጥ ነበር። እነርሱም “መልአኩ ነው፤” አሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እነርሱም “አብደሻል!” አሉአት። እርስዋ ግን “በእውነት እርሱ ነው!” ስትል አረጋገጠች፤ እነርሱም እንግዲያውስ “የእርሱ ጠባቂ መልአክ ይሆናል” አሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እነ​ር​ሱም “አብ​ደ​ሻ​ልን? አንድ ጊዜ ታገሺ” አሉ​አት፤ እር​ስዋ ግን እርሱ እንደ ሆነ ታረ​ጋ​ግጥ ነበር። እነ​ር​ሱም፥ “ምና​ል​ባት መል​አኩ ይሆ​ናል” አሉ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 12:15
10 交叉引用  

እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምን የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ በምድርም መካከል ይብዙ።


ብጠራው እርሱም ቢመልስልኝ ኖሮ፥ ቃሌን እንደ ሰማ አላምንም ነበር።


ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።


እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም።


ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ፥ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ።


አንድ ሰዓትም የሚያህል ቆይቶ ሌላው አስረግጦ፦ እርሱ የገሊላ ሰው ነውና በእውነት ይህ ደግሞ ከእርሱ ጋር ነበረ አለ።


ይህም ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸውና አላመኑአቸውም።


ጴጥሮስ ግን ማንኳኳቱን አዘወተረ፤ ከፍተውም አዩትና ተገረሙ።


እንዲህም ብሎ ስለ ራሱ ሲመልስ ፊስጦስ በታላቅ ድምፅ፦ “ጳውሎስ ሆይ፥ አብድሃል እኮ፤ ብዙ ትምህርትህ ወደ እብደት ያዞርሃል” አለው።


跟着我们:

广告


广告