Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ዳዊትም፦ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሃለሁና አትፍራ፥ የአባትህንም የሳኦልን ምድር ሁሉ እመልስልሃለሁ፥ አንተም ሁልጊዜ ከገበታዬ እንጀራ ትበላለህ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ዳዊትም፣ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል በርግጥ ቸርነት አደርግልሃለሁና። የአባትህን የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከማዕዴ ትበላለህ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ዳዊትም፥ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግልሃለሁ። የአባትህን የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከማዕዴ ትበላለህ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ዳዊትም “አይዞህ አትፍራ! ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግልሃለሁ፤ የአያትህ የሳኦል ይዞታ የነበረውን መሬት ሁሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም በማእዴ ተቀምጠህ ትመገባለህ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ዳዊ​ትም፥ “ስለ አባ​ትህ ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት ፈጽሜ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ የአ​ባ​ት​ህን አባት የሳ​ኦ​ልን መሬት ሁሉ እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ሁል ጊዜ ከገ​በ​ታዬ እን​ጀ​ራን ትበ​ላ​ለህ” አለው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 9:7
32 交叉引用  

እነርሱም ወደ ዮሴፍ ቤት ስለ ገቡ ፈሩ እንዲህም አሉ፦ በዓይበታችን ቀድሞ ስለ ተመለሰው ብር ሊተነኮልብን ሊወድቅብንም እኛንም በባርነት ሊገዛ አህዮቻችንንም ሊወስድ ወደዚህ አስገባን።


እርሱም አላቸው፦ ስላም ለእናንተ ይሁን አትፍሩ አምላካችሁና የአባታችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ ብራችሁስ ደርሶኛል።


የጌታህን ቤት ሰጠሁህ፥ የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፥ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።


የአባቴ ቤት ሁሉ በጌታዬ በንጉሡ ዘንድ ሞት የሚገባቸው ነበሩ፥ አንተ ግን እኔን ባሪያህን በገበታህ በሚበሉ መካከል አስቀመጥኸኝ፥ ለንጉሥ ደግሞ ለመናገር ምን መብት አለኝ?


ንጉሡም፦ ነገርህን ለምን ታበዛለህ? አንተና ሲባ እርሻውን ትካፈሉ ዘንድ ብያለሁ አለው።


ንጉሡም ቤርዜሊን፦ በኢየሩሳሌም እቀልብህ ዘንድ ከእኔ ጋር እለፍ አለው።


ንጉሡም በሳኦል ልጅ በዮናታንና በዳዊት መካከል ስለ ነበረው ስለ እግዚአብሔር መሐላ የሳኦልን ልጅ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን አዳነ።


ዳዊትም፦ ስለ ዮናታን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት አንድ ሰው ቀርቶአልን? አለ።


አንተና ልጆችህ ሎሌዎችህም ምድሩን እረሱለት፥ ለጌታህም ልጅ እንጀራ ይሆነው ዘንድ ፍሬውን አግባ፥ የጌታህ ልጅ ሜምፊቦስቴ ግን ሁልጊዜ ከገበታዬ ይበላል አለው። ለሲባም አሥራ አምስት ልጆችና ሀያ ባሪያዎች ነበሩት።


ሲባም ንጉሡን፦ ጌታዬ ንጉሡ ባሪያውን እንዳዘዘ እንዲሁ ባሪያህ ያደርጋል አለው። ሜምፊቦስቴም ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳዊት ገበታ ይበላ ነበር።


ሜምፊቦስቴም ከንጉሥ ገበታ ሁልጊዜ እየበላ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ነበር፥ ሁለት እግሩም ሽባ ነበረ።


ንጉሡም፦ የእግዚአብሔርን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት አንድ ሰው አልቀረምን? አለ። ሲባም ንጉሡን፦ እግሩ ሽባ የሆነ አንድ የዮናታን ልጅ አለ አለው።


ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ ቀርበውኛልና ለገለዓዳዊው ለቤርዜሊ ልጆች መልካም ቸርነት አድርግላቸው፤ በማዕድህም ከሚበሉት መካከል ይሁኑ።


በወህኒም ውስጥ ለብሶት የነበረውን ልብስ ለወጠለት፤ ዮአኪንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በፊቱ ሁልጊዜ እንጀራ ይበላ ነበር።


በወህኒም ውስጥ ለብሶት የነበረውን ልብስ ለወጠለት፥ ዮአኪንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በፊቴ ሁልጊዜ እንጀራ ይበላ ነበር።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፥ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፥ መበለቲቱንና ደሀ አደጉን፥


የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤


እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።


ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ያደረገላችሁንም ታላቅ ነገር አይታችኋልና በፍጹም ልባችሁ በእውነት አምልኩት።


ደግሞም እግዚአብሔር የዳዊትን ጠላቶች ሁሉ እያንዳንዱ ከምድር ባጠፋቸው ጊዜ ለዘላለም ቸርነትህን ከቤቴ አታርቀው።


ነፍሴን የሚፈልግ የአንተን ነፍስ ይፈልጋልና፥ ከእኔም ጋር ተጠብቀህ ትኖራለህና በእኔ ዘንድ ተቀመጥ፥ አትፍራ አለው።


跟着我们:

广告


广告