Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 9:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ንጉሡም፦ የእግዚአብሔርን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት አንድ ሰው አልቀረምን? አለ። ሲባም ንጉሡን፦ እግሩ ሽባ የሆነ አንድ የዮናታን ልጅ አለ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ንጉሡም፣ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” ሲል ጠየቀው። ሲባም ለንጉሡ፣ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ንጉሡም፥ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” ሲል ጠየቀው። ጺባም ለንጉሡ፥ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ንጉሡም “እግዚአብሔር የሚፈቅደውን ቸርነት የማሳየው ከሳኦል ቤተሰብ ከሞት የተረፈ ሰው አለን?” ሲል ጺባን ጠየቀው። ጺባም “ከዮናታን ወንዶች ልጆች አንዱ አሁንም በሕይወት አለ፤ እርሱም እግረ ሽባ ነው” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ንጉ​ሡም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነት አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ ከሳ​ኦል ቤት የቀረ ሰው አለን?” አለ። ሲባም ንጉ​ሡን፥ “እግ​ሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮ​ና​ታን ልጅ አለ” አለው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 9:3
11 交叉引用  

እርሱም መልሶ አለ፦ ጌታዬ፥ ንጉሥ ሆይ፥ ባሪያዬ አታለለኝ፥ እኔ ባሪያህ አንካሳ ነኝና፦ ከንጉሥ ጋር እሄድ ዘንድ የምቀመጥበትን አህያ ልጫን አልሁት።


እርሱም እኔን ባሪያህን ለጌታዬ ለንጉሡ አማ፥ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፥ ደስም ያሰኘህን አድርግ።


ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፥ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፥ ፈጥናም ስትሸሽ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፊቦስቴ ነበረ።


ሜምፊቦስቴም ከንጉሥ ገበታ ሁልጊዜ እየበላ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ነበር፥ ሁለት እግሩም ሽባ ነበረ።


ዳዊትም፦ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሃለሁና አትፍራ፥ የአባትህንም የሳኦልን ምድር ሁሉ እመልስልሃለሁ፥ አንተም ሁልጊዜ ከገበታዬ እንጀራ ትበላለህ አለው።


አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ ርኅሩኆች ሁኑ።


ብቻ እግዚአብሔር ስለ አባቶችህ ደስ ብሎታል፥ እነርሱንም ወድዶአል፤ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራቸውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መረጠ።


አባቶችህን ወድዶአልና ከእነርሱ በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ የጸኑትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊትህ እንዲያወጣ፥ አንተንም እንዲያገባህ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ እንዲሰጥህ፥ ከአንተ ጋር ሆኖ በታላቅ ኃይሉ ከግብፅ አወጣህ።


跟着我们:

广告


广告