Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 8:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ንጉሡም ዳዊት ከአድርአዛር ከተሞች ከቤጣሕና ከቤሮታይ እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ንጉሡ ዳዊት ቤጣህና ቤሮታይ ከተባሉ ከአድርአዛር ከተሞችም እጅግ ብዙ ናስ አጋዘ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ንጉሡ ዳዊት ቤጣህና ቤሮታይ ከተባሉ ከሀዳድዔዜር ከተሞችም እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እንዲሁም ንጉሥ ዳዊት ሀዳድዔዜር ከሚያስተዳድራቸው ቤጣሕና ቤሮታይ ተብለው ከሚጠሩት ከተሞች እጅግ ብዙ የሆነ ነሐስ ወሰደ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ንጉ​ሡም ዳዊት ከሶ​ቤ​ቅና ከተ​መ​ረ​ጡት ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ከተ​ሞች እጅግ ብዙ ናስን ወሰደ። በእ​ር​ሱም ሰሎ​ሞን የብ​ረት ባሕ​ርና ምሰ​ሶ​ዎ​ችን፥ ሰኖ​ች​ንና ሌሎች ዕቃ​ዎ​ችን ሠራ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 8:8
9 交叉引用  

ዳዊትም ለአድርአዛር ባሪያዎች የነበሩትን የወርቅ ጋሾች ወሰደ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞአቸው መጣ።


እግዚአብሔርም ደግሞ ከጌታው ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር የኰበለለውን የኤልያዳን ልጅ ሬዞንን ጠላት አድርጎ አስነሣበት።


ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፤ አዋረዳቸውም፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ጌትንና መንደሮችዋን ወሰደ።


ከአድርአዛርም ከተሞች ከጢብሐትና ከኩን ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚህም ሰሎሞን የናሱን ኵሬና ዐምዶች የናሱንም ዕቃ ሠራ።


አሁንም፥ እነሆ በምችለው ለእግዚአብሔር ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት አዘጋጀሁ፤ ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፤ አንተም ከዚያ በላይ ጨምር።


የሚሠሩበት ወርቅና ብር ናስና ብረት ቍጥር የለውም፤ ተነሥተህ ሥራ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን።”


ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት አምስት ሺህ መክሊት ወርቅና ዐሥር ሺህ ዳሪክ፥ ዐሥር ሺህም መክሊት ብር፥ ዐሥራ ስምንት ሺህም መክሊት ናስ፥ መቶ ሺህም መክሊት ብረት ሰጡ።


ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደማስቆ ድንበርና በሐማት ድንበር መካከል ያለው ሲብራይም፥ በሐውራን ድንበር አጠገብ ያለው ሐጸርሃቲኮን።


跟着我们:

广告


广告