Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 8:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፥ ዳዊትም ለሕዝቡ ሁሉ ፍርድንና ጽድቅን አደረገላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕና ርትዕ አሰፈነላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስለዚህ ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ትክክለኛ ፍርድ አሰፈነላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በዚህ ዐይነት ዳዊት የመላው እስራኤል ንጉሥ ሆኖ ሕዝቡ ዘወትር ትክክለኛ ፍርድ ማግኘት እንዲችል ጥረት ያደርግ ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ዳዊ​ትም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 8:15
24 交叉引用  

አቤሴሎምም፦ ነገርህ እውነትና ቅን ነው፥ ነገር ግን ከንጉሥ ታዝዞ የሚሰማህ የለም ይለው ነበር።


ኢዮአብም በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበር፥ የዩዳሄም ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፥


አበኔርም ለዳዊት፦ ምድሪቱ ለማን ናት? ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እጄም ከአንተ ጋር ትሆናለች፥ እስራኤልንም ሁሉ ወደ አንተ እመልሰዋለሁ ብለው ይነግሩት ዘንድ መልእክተኞች ሰደደለት።


በኬብሮን በይሁዳ ላይ ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነገሠ፥ በኢየሩሳሌምም በእስራኤል ሁሉና በይሁዳ ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።


በኤዶምያስ ሁሉ ጭፍሮች አኖረ፥ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ እግዚአብሔርም ዳዊት በሚሄድበት ሁሉ ድልን ሰጠው።


የጽሩያ ልጅ ኢዮአብም የሠራዊት አለቃ ነበረ፥ የአሒሉድም ልጅ ኢዮሣፍጥ ታሪክ ጸሐፊ ነበረ፥


አንተን የወደደ፥ በእስራኤልም ዙፋን ያስቀመጠህ አምላክ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን! እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘላለም ወድዶታልና፥ ስለዚህ ጽድቅና ፍርድ ታደርግ ዘንድ ንጉሥ አድርጎ አስነሣህ።”


ንጉሡም ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር።


ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ፍርድንና ጽድቅን አደረገላቸው።


ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።


ክፉውን ጥሉ፥ መልካሙንም ውደዱ፥ በበሩም አደባባይ ፍርድን አጽኑ፥ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል።


ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ።


እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥


ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፥ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ይዋጋ ነበር፥ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።


跟着我们:

广告


广告