Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 7:23 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ፥ በአሕዛብና በአምላኮቻቸውም ፊት ከግብጽ በተቤዠው ሕዝብ ፊት ተአምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ሄደለት እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፣ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፣ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክታቸውን ከፊቱ አሳድዶ ታላላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፥ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፥ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክቶቻቸውን ከፊቱ አሳዶ ታላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ያድን ዘንድ፥ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ፥ ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን ያደርግ ዘንድ፥ ሕዝቦችንና አማልክቶቻቸውን በፊታቸው ያስወግድ ዘንድ እግዚአብሔር ከግብጽ ባርነት እንዳዳነው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ለእ​ርሱ ለራሱ እን​ዲ​ሆን ሕዝ​ብን ይቤዥ ዘንድ ለእ​ርሱ ለራ​ሱም ታላቅ ስምን ያደ​ርግ ዘንድ አሕ​ዛ​ብ​ንና ሰፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን በመ​በ​ተን ከግ​ብፅ በተ​ቤ​ዠ​ኸው ሕዝ​ብህ ፊት ታም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መራው እንደ ሕዝ​ብህ እንደ እስ​ራ​ኤል ያለ በም​ድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 7:23
36 交叉引用  

ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘላለም ሕዝብ አድርገህ አጽንተኸዋል፥ አንተም፥ አቤቱ፥ አምላክ ሆነሃቸዋል።


አንተ እግዚአብሔር ከግብጽ ካወጣኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብን በማሳደድ በታላቅና በሚያስፈራ ነገር ለአንተ ስም ታደርግ ዘንድ፥ ለአንተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደ ሄድህለት እንደ አንተ ሕዝብ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ አለን?


እነዚህም በታላቅ ኃይልህና በብርቱ እጅህ የተቤዠሃቸው ባሪያዎችህና ሕዝብህ ናቸው።


እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፤ በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ የተለየን እንሆን ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? አለው።


ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፤ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


አሁን እጄን ዘርግቼ አንተን ሕዝብህንም በቸነፈር በመታሁህ ነበር፤ አንተም ከምድር በጠፋህ ነበር፤


ነገር ግን ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ።


እስከ ዛሬም ድረስ ምልክትንና ድንቅን ነገር በግብጽ ምድር ደግሞም በእስራኤልና በሌሎች ሰዎች መካከል አድርገሃል፥ እንደ ዛሬም ለአንተ ስም አድርገሃል።


በምልክትና በድንቅ ነገር፥ በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ በታላቅም ግርማ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብጽ ምድር አወጣህ።


ነገር ግን በመካከላቸው ባሉ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


እንዲሁ ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።


በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ።


ዓይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቆች የሚያስፈሩትንም ነገሮች ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱም አምላክህ ነው።


አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበርህ አምላክህም እግዚአብሔር እንዳዳነህ አስብ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝዝሃለሁ።


እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤ 2 በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? 2 እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ 2 የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። 2 ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤ 2 አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።


በእግዚአብሔርም ፊት እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ በታላቅነትህ የተቤዠኸውን፥ በጠነከረችውም እጅ ከግብፅ ያወጣኸውን ሕዝብህንና ርስትህን አታጥፋ።


መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ከነዓናውያንም በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ሰምተው ይከብቡናል፥ ስማችንንም ከምድር ያጠፋሉ፥ ለታላቁ ስምህም የምታደርገው ምንድር ነው?


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


跟着我们:

广告


广告