Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 7:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እተክለውማለሁ፥ በስፍራውም ይቀመጣል፥ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፥ እንደ ቀድሞው ዘመንና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፈራጆች እንዳስነሣሁበት ጊዜ ግፈኞች ተመልሰው አያስጨንቁትም፥ ከጠላቶችህም አሳርፍሃለሁ። እግዚአብሔርም ደግሞ፦ ቤት እሠራልሃለሁ ብሎ ይነግርሃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ለሕዝቤ ለእስራኤልም መሪዎች ከሾምሁለት ጊዜ አንሥቶ ያደረጉትን ዛሬ አያደርጉበትም፤ እንዲሁም ከጠላቶችህ ሁሉ እጠብቅሃለሁ። “ ‘እግዚአብሔር ራሱ ቤት እንደሚሠራልህ ይነግርሃል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ለሕዝቤ ለእስራኤል መሪዎች ከሾምሁለት ጊዜ አንሥቶ እንዳደረጉበት ከእንግዲህ አያደርጉበትም፤ ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ። ከዚህም በላይ ጌታ ራሱ ቤት እንደሚሠራልህ ይነግርሃል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆ​ችን በሾ​ምሁ ጊዜ ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ሁሉ አሳ​ር​ፍ​ሃ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ፦ ቤት እን​ደ​ም​ት​ሠ​ራ​ለት ይነ​ግ​ር​ሃል፤ እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 7:11
20 交叉引用  

እንዲህም ሆነ፥ ንጉሡ በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ እግዚአብሔርም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ባሳረፈው ጊዜ፥


ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፥ ስለ ባሪያህም ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፥ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህ የሰው ሕግ ነው።


አቤቱ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ አንተ፦ እኔ ቤት እሠራልሃለሁ ብለህ ለባሪያህ ገልጠሃልና ስለዚህ ባሪያህ ይህችን ጸሎት ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ በልቡ ደፈረ።


ባሪያዬም ዳዊት እንዳደረገ፥ ያዘዝሁህን ሁሉ ብትሰማ፥ በመንገዴም ብትሄድ፥ በፊቴም የቀናውን ብታደርግ፥ ሥርዐቴንና ትእዛዜን ብትጠብቅ፥ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ለዳዊትም እንደ ሠራሁለት ጽኑ ቤት እሠራልሃለሁ፤ እስራኤልንም ለአንተ እሰጥሃለሁ።


አሁንም ያጸናኝ፥ በአባቴም በዳዊት ዙፋን ላይ ያስቀመጠኝ፥ እንደ ተናገረውም ቤትን የሠራልኝ ሕያው እግዚአብሔርን! ዛሬ አዶንያስ ፈጽሞ ይገደላል፤” ብሎ በእግዚአብሔር ማለ።


እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፤ ልጅም ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ የመንግሥቱንም ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’


በሕዝብ ወይም በሰው ዘንድ ቢሆን፥ እርሱ ቢያሳርፍ የሚፈርድ ማን ነው? ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?


እንዲህም ሆነ፤ አዋላጆች እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ ቤተሰብን ሰጣቸው።


እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥


የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፥ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።


የእግዚአብሔርን ጦርነት ስለምትዋጋ እግዚአብሔር በእውነት ለጌታዬ የታመነ ቤት ይሠራልና የእኔን የባሪያህን ኃጢአት፥ እባክህ፥ ይቅር በል፥ በዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህም።


跟着我们:

广告


广告