2 ሳሙኤል 6:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ በይሁዳ ካለች ከበኣል ተነሥተው በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ያመጡ ዘንድ ሄዱ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እርሱና ዐብረውት ያሉት ሰዎች ሁሉ በታቦቱ ላይ ባለው ኪሩቤል ላይ በተቀመጠው በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔርም ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው ወደ ባኣላ ሄዱ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው በዓል ሄዱ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በኪሩቤል ላይ ዙፋኑን የዘረጋውን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የቃል ኪዳኑን ታቦት ለማምጣት ወደ በዓለ ይሁዳ ሄዱ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ከይሁዳ አለቆች ጋር ተነሥተው በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም የተጠራባትን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ያመጡ ዘንድ ሄዱ። 参见章节 |