Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 6:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በገባ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፥ ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልልና ሲዘፍን አየች፥ በልብዋም ናቀችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ፣ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ትመለከት ነበር፤ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልልና ሲያሸበሽብ ባየችው ጊዜ በልቧ ናቀችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የጌታ ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ፥ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ትመለከት ነበር፤ ንጉሥ ዳዊት በጌታ ፊት ሲዘልና ሲያሸበሽብ ባየችው ጊዜ በልቧ ናቀችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ታቦቱን ይዘው ወደ ከተማ በሚገቡበት ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ተመለከተች፤ ንጉሡ ዳዊት እየዘለለ ሲያሸበሽብ አይታም በልብዋ ናቀችው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ረ​ሰች ጊዜ የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮል በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ንጉ​ሡም ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሲዘ​ል​ልና ሲዘ​ምር አየ​ችው፥ በል​ብ​ዋም ናቀ​ችው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 6:16
12 交叉引用  

ዳዊትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ፦ በመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ያጨኋትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ ብሎ መልእክተኞችን ሰደደ።


ነገር ግን ዳዊት አምባይቱን ጽዮንን ያዘ፥ እርስዋም የዳዊት ከተማ ናት።


ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ ሆ እያሉ ቀንደ መለከትም እየነፋ የእግዚአብሔርን ታቦት አመጡ።


ዳዊትም ቤተ ሰቡን ሊመርቅ ተመለሰ። የሳኦልም ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ለመቀበል ወጣችና፦ ምናምንቴዎች እርቃናቸውን እንደሚገልጡ የእስራኤል ንጉሥ በባሪያዎቹ ቈነጃጅት ፊት እርቃኑን በመግለጡ ምንኛ የተከበረ ነው! አለችው።


የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት ሲዘፍንና ሲጫወት አይታ በልብዋ ናቀችው።


የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፥ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።


ሌሎች ግን እያፌዙባቸው፦ “ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል” አሉ።


ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።


ሳኦልም ዳዊትን፦ ታላቂቱ ልጄ ሜሮብ እነኋት፥ እርስዋን እድርልሃለሁ፥ ብቻ ቀልጣፋ ልጅ ሁንልኝ፥ ስለ እግዚአብሔርም ጦርነት ተጋደል አለው። ሳኦልም፦ የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእርሱ ላይ አትሁን ይል ነበር።


የሳኦልም ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደች፥ ይህም ወሬ ለሳኦል ደረሰለት፥ ነገሩም ደስ አሰኘው።


跟着我们:

广告


广告