Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዳዊትም በአምባይቱ ውስጥ ተቀመጠ፥ የዳዊትም ከተማ ብሎ ጠራት። ዳዊትም ዙሪያዋን ከሚሎ ጀምሮ ወደ ውስጥ ቀጠራት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐምባዪቱ ላይ አደረገ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራት። ዳዊትም ከሚሎ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ገነባት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በምሽጉ ላይ አደረገ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራው። ዳዊትም ከሚሎ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ገነባው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ዳዊት ምሽጉን ከያዘ በኋላ መኖሪያውን በዚያው ስፍራ አደረገ፤ እርስዋንም “የዳዊት ከተማ” ብሎ ጠራት፤ ከኮረብታው በስተ ምሥራቅ በኩል በዐፈር ከተደለደለው ስፍራ አንሥቶ በኮረብታው ዙሪያ ከተማይቱንም ሠራ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዳዊ​ትም በአ​ን​ባ​ዪቱ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ተባ​ለች። ከተ​ማ​ዋ​ንም ዙሪ​ያ​ዋን እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ቀጠ​ራት፤ ቤቱ​ንም ሠራ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 5:9
16 交叉引用  

ነገር ግን ዳዊት አምባይቱን ጽዮንን ያዘ፥ እርስዋም የዳዊት ከተማ ናት።


በዚያም ቀን ዳዊት፦ ኢያቡሳውያንን የሚመታ በውኃ መሄጃው ይውጣ፥ የዳዊትም ነፍስ የምትጠላቸውን ዕውሮችንና አንካሶችን ያውጣ አለ። ስለዚህም በምሳሌ፦ ዕውርና አንካሳ ወደ ቤት አይግቡ ተባለ።


ዳዊትም የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመጣው ዘንድ አልወደደም፥ ዳዊትም በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት አገባው።


በንጉሡም ያመፀበት ምክንያት ይህ ነው፤ ሰሎሞን ሚሎን ሠራ፤ የአባቱንም የዳዊትን ከተማ ሰባራውን ጠገነ።


ዳዊትም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ።


ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት፥ ሚሎንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ ሐጾርንም፥ መጊዶንም፥ ጌዝርንም ይሠራ ዘንድ ገባሮችን መልምሎ ነበር።


የፈርዖንም ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ወደ ቤትዋ ወጣች፤ በዚያን ጊዜም ሚሎን ሠራ።


የቀረውም የኢዮአስ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?


ባሪያዎቹም ተነሥተው ዐመፁበት፤ ወደ ሲላ በሚወርደውም መንገድ በሚሎ ቤት ገደሉት።


ከሚሎም ጀምሮ በዙሪያው ከተማ ሠራ፤ ኢዮአብም የቀረውን ከተማ አበጀ።


ሰውነቱንም አጸናና፥ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ግንብ ሠራበት፤ ከእርሱም በስተ ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ በዳዊትም ከተማ ያለችውን ሚሎን አጠነከረ፤ ብዙም መሣሪያና ጋሻ ሠራ።


የምጽጳም ግዛት አለቃ የኮልሖዜ ልጅ ሰሎም የምንጩን በር አደሰ፥ ሠራው፥ ከደነውም፥ ሳንቃዎቹንም አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ፥ ከዳዊትም ከተማ እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ያለውን የሼላን መዋኛ ቅጥር ሠራ።


ዳዊት ለሰፈረባት ከተማ ለአርኤል ወዮላት! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሩ፥ በዓላትም ይመለሱ።


እንዲህ ባይሆን ግን ከአቤሜሌክ እሳት ይውጣ፥ የሴኬምንም ሰዎች ቤትሚሎንም ይብላ፥ ከሴኬምም ሰዎች ከቤትሚሎም እሳት ይውጣ፥ አቤሜሌክንም ይብላ።


የሴኬምም ሰዎች ሁሉ ቤትሚሎም ሁሉ ተሰበሰቡ፥ ሄደውም በሴኬም በዓምዱ አጠገብ ባለው በአድባሩ ዛፍ በታች አቤሜሌክን አነገሡ።


跟着我们:

广告


广告