Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 5:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የእስራኤልም ነገድ ሁሉ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው፦ እነሆ፥ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቁራጭ ነን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉ፤ “እነሆ፤ እኛ የዐጥንትህ ፍላጭ፣ የሥጋህ ቍራጭ ነን፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉ፤ “እነሆ እኛ የዐጥንትህ ፍላጭ፥ የሥጋህ ቁራጭ ነን፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ በኬብሮን ወደነበረው ወደ ዳዊት ሄደው እንዲህ አሉት፦ “እነሆ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ፥ የሥጋህ ቊራጭ የሆንን ወገኖችህ ነን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ወደ ኬብ​ሮን ወደ ዳዊት መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እኛ የአ​ጥ​ን​ትህ ፍላጭ የሥ​ጋህ ቍራጭ ነን።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 5:1
13 交叉引用  

ላባም፦ በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ።


እናንተ ወንድሞቼ፥ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቁራጭ ናችሁ፥ እናንተ ንጉሡን ከመመለስ ስለ ምን ዘገያችሁ?


ለአሜሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቁራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።


የይሁዳንም ሰዎች ሁሉ ልብ እንደ አንድ ሰው ልብ አድርጎ አዘነበለ፥ ወደ ንጉሡም ልከው፦ አንተ ከባሪያዎችህ ሁሉ ጋር ተመለስ አሉት።


የእስራኤልም ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች መልሰው፦ በንጉሡ ዘንድ ለእኛ አሥር ክፍል አለን፥ በዳዊትም ዘንድ ደግሞ ከእናንተ ይልቅ መብት አለን፥ ስለ ምን ናቃችሁን? ስለ ምንስ ንጉሣችንን ለመመለስ ቀድሞ ምክር አልጠየቃችሁንም? አሉ። የይሁዳም ሰዎች ቃል ከእስራኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነከረ።


አሣሄልንም አንሥተው በቤተ ልሔም በአባቱ መቃብር ቀበሩት፥ ኢዮአብና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ፥ በኬብሮንም አነጉ።


አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን በላይህ ታነግሣለህ፤ ከወንድሞችህ መካከል የሆነውን በአንተ ላይ ንጉሥ ታነግሣለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ከሌላ ወገን ሰው በላይህ ንጉሥ ታደርግ ዘንድ አይገባህም።


እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።


ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከኦዶላም ወደ ኬብሮን ወጡ፥ ወጉአትም፥ ያዙአትም፥


በሴኬም ሰዎች ሁሉ ጆሮ፦ ሰባ የሆኑት የይሩበኣል ልጆች ሁሉ ቢገዙአችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገዛችሁ ምን ይሻላችኋል? ብላችሁ ንገሩአቸው ብዬ እለምናችኋለሁ፥ ደግሞ እኔ የአጥንታችሁ ፍላጭ የሥጋችሁ ቁራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ ብሎ ተናገራቸው።


跟着我们:

广告


广告