Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 4:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በረኛይቱም ስንዴ ታበጥር ነበር፥ አንቀላፍታም ተኝታ ነበር፥ ሬካብና ወንድሙ በዓናም በቀስታ ገቡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስንዴ እንደሚፈልግም ሰው ሆነው ወደ ቤቱ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ሆዱ ላይ ወጉት። ከዚያም ሬካብና ወንድሙ በዓና ሹልክ ብለው ወጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እነሆም ስንዴ እንደሚፈልግም ሰው ሆነው ወደ ቤቱ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ሆዱ ላይ ወጉት። ከዚያም ሬካብና ወንድሙ በዓና አመለጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ጠባቂዋ ሴት ስንዴ እያበጠረች በበር ላይ ተቀምጣ ታንቀላፋ ነበር፤ ስለዚህም ሬካብና በዓና በቀስታ አልፈው ገቡ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በረ​ኛ​ዪ​ቱም ስንዴ ታበ​ጥር ነበር፤ አን​ቀ​ላ​ፍ​ታም ተኝታ ነበር፤ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾቹ ሬካ​ብና በዓ​ናም በቀ​ስታ ወደ ቤት ገቡ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 4:6
5 交叉引用  

ነገር ግን ከእርሱ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ፥ አበኔርም በጦሩ ጫፍ ሆዱን ወጋው፥ ጦሩም በኋላው ወጣ፥ በዚያም ስፍራ ወድቆ ሞተ። አሣሄልም ወድቆ በሞተበቱ ስፍራ የሚያልፍ ሁሉ ይቆም ነበር።


አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፥ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፥ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፥ ሁለተኛም አልወጋውም፥ ሞተም።


አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቆይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፥ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ሆዱን መታው፥ ሞተም።


ለሳኦልም ልጅ ለኢያቡስቴ የጭፍራ አለቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፥ የአንዱም ስም በዓና፥ የሁለተኛውም ስም ሬካብ ነበረ፥ ከብንያምም ልጆች የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ነበሩ፥ ብኤሮትም ለብንያም ተቆጥራ ነበር።


በዘገዩበትም ጊዜያት ናዖድ ሸሸ፥ ትክል ድንጋዮቹንም አለፈ፥ ወደ ሴይሮታም አመለጠ።


跟着我们:

广告


广告