Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 4:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፥ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፥ ፈጥናም ስትሸሽ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፊቦስቴ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው። እርሱም የሳኦልና የዮናታን አሟሟት ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የዐምስት ዓመት ልጅ ነበረ። ሽባ የሆነውንም በዚህ ጊዜ ሞግዚቱ አንሥታው በጥድፊያ ስትሸሽ በመውደቁ ነው። ስሙም ሜምፊቦስቴ ይባል ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው። እርሱም የሳኦልና የዮናታን አሟሟት ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ። ሽባ የሆነውንም በዚህ ጊዜ ሞግዚቱ አንሥታው በጥድፊያ ስትሸሽ በመውደቁ ነው። ስሙም መፊቦሼት ይባል ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሌላው የሳኦል ዘር የዮናታን ልጅ መፊቦሼት ሲሆን፥ እርሱ ሳኦልና ዮናታን በተገደሉ ጊዜ ገና የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፤ የእነርሱን ሞት የሚገልጠው ወሬ ከኢይዝራኤል ከተማ በተነገረ ጊዜ ሞግዚቱ እርሱን ይዛ ሸሸች፤ ነገር ግን በጥድፍያ በምትሸሽበት ጊዜ ከእጅዋ ወደቀ፤ ከዚህም የተነሣ ሽባ ሆነ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለዮ​ና​ታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበ​ረው። የሳ​ኦ​ልና የዮ​ና​ታን ወሬ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል በመጣ ጊዜ የአ​ም​ስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግ​ዚ​ቱም አዝ​ላው ሸሸች፤ ልት​ሸ​ሽም ስት​ሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ነበረ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 4:4
10 交叉引用  

ንጉሡም በሳኦል ልጅ በዮናታንና በዳዊት መካከል ስለ ነበረው ስለ እግዚአብሔር መሐላ የሳኦልን ልጅ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን አዳነ።


ሜምፊቦስቴም ከንጉሥ ገበታ ሁልጊዜ እየበላ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ነበር፥ ሁለት እግሩም ሽባ ነበረ።


ንጉሡም፦ የእግዚአብሔርን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት አንድ ሰው አልቀረምን? አለ። ሲባም ንጉሡን፦ እግሩ ሽባ የሆነ አንድ የዮናታን ልጅ አለ አለው።


የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት መጣ፥ በግምባሩም ወድቆ እጅ ነሣ፥ ዳዊትም፦ ሜምፊቦስቴ ሆይ፥ አለ፥ እርሱም፦ እነሆኝ ባሪያህ አለ።


ሃዳድ ገና ብላቴና ሳለ ሃዳድና ከእርሱ ጋር ጥቂቶቹ ከኤዶምያስ ሰዎች የሆኑ የአባቱ ባሪያዎች ወደ ግብጽ ኰብልለው ነበር።


የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ።


የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ።


ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበሰቡ፥ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።


ዳዊትና ሰዎቹም ማልደው ይሄዱ ዘንድ፥ ወደ ፍልስጥኤማውያንም አገር ይመለሱ ዘንድ ተነሡ። ፍልስጥኤማውያንም ወደ ኢይዝራኤል ወጡ።


跟着我们:

广告


广告