Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ይልቁንስ በቤቱ ውስጥ በምንጣፋ ላይ ንጹሑን ሰው የገደላችሁትን እናንተን ኃጢአተኞችንማ እንዴት ነዋ? ደሙን ከእጃችሁ አልሻውምን? ከምድርም አላጠፋችሁምን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ታዲያ በገዛ ቤቱ፣ በገዛ ዐልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው የገደሉትን ክፉ ሰዎች እንዴት የባሰ ቅጣት አይገባቸውም? ደሙን ከእጃችሁ መፈለግ፣ እናንተን ከምድሪቱ ማጥፋት የለብኝምን?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ታዲያ በገዛ ቤቱ፥ በገዛ አልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው የገደሉትን ክፉ ሰዎች እንዴት የባሰ ቅጣት አይገባቸውም? ደሙን ከእጃችሁ መፈለግ፥ እናንተን ከምድሪቱ ማጥፋት የለብኝምን?”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ታዲያ፥ በገዛ ቤቱ ተኝቶ የነበረውን ንጹሕ ሰው ለገደሉት ሰዎችማ የሚከፈላቸው የበቀል ዋጋ ምን ያኽል የከፋ ይሆን? ስለዚህም እርሱን በመግደላችሁ ምክንያት እኔ በእናንተ ላይ የበቀል እርምጃ በመውሰድ ከምድር ላይ ጠራርጌ አጠፋችኋለሁ!”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አሁ​ንም እና​ንተ ክፉ​ዎች ሰዎች በቤቱ ውስጥ በአ​ል​ጋው ላይ ጻድ​ቁን ሰው ገደ​ላ​ች​ሁት፤ እነሆ፥ ደሙን ከእ​ጃ​ችሁ እሻ​ለሁ፤ ከም​ድ​ርም አጠ​ፋ​ች​ኋ​ለሁ።”

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 4:11
19 交叉引用  

አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፍተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።


እግዚእብሔርም ኖኅን አለው፤ የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችን እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።


በምድር ላይ የነበውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ፤ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፤ እስከ ሰማይ ወፍ ድረስ ተደመሰሰ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ።


በፋንታው ነግሠሃልና እግዚአብሔር የሳኦልን ቤት ደም ሁሉ መለሰብህ፥ እግዚአብሔርም መንግሥትን ለልጅህ ለአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቶታል፥ እነሆም፥ አንተ የደም ሰው ነህና በመከራ ተይዘሃል አለ።


አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቆይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፥ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ሆዱን መታው፥ ሞተም።


እኔም ዛሬ ምንም ለመንገሥ የተቀባሁ ብሆን ደካማ ነኝ፥ እነዚህም ሰዎች የጽሩያም ልጆች በርትተውብኛል፥ እግዚአብሔር ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት አላቸው።


አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእርሱ የሚሻሉትን ሁለቱን ጻድቃን ሰዎች፥ የእስራኤልን ሠራዊት አለቃ የኔርን ልጅ አበኔርን፥ የይሁዳንም ሠራዊት አለቃ የዬቴርን ልጅ አሜሳይን፥ በሰይፍ ገድሎአልና እግዚአብሔር ደሙን በራሱ ላይ ይመልሰው።


ሰው ሰውን ቢመታ ቢሞትም፥ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።


አሁን እጄን ዘርግቼ አንተን ሕዝብህንም በቸነፈር በመታሁህ ነበር፤ አንተም ከምድር በጠፋህ ነበር፤


እናንተም፦ ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ ትሉአቸዋላችሁ።


አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፥ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል።


ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፥ ፍርድም ድል ነሥቶ አይወጣም፥ ኃጢአተኛ ጻድቅን ይከብባልና፥ ስለዚህ ፍርድ ጠማማ ሆኖ ይወጣል።


ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።


跟着我们:

广告


广告