Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 3:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አበኔርም ለዳዊት፦ ምድሪቱ ለማን ናት? ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እጄም ከአንተ ጋር ትሆናለች፥ እስራኤልንም ሁሉ ወደ አንተ እመልሰዋለሁ ብለው ይነግሩት ዘንድ መልእክተኞች ሰደደለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከዚያም አበኔር ለዳዊት፣ “ምድሪቱ የማን ናት? ከእኔ ጋራ ተስማማ፤ እነሆ እስራኤል ሁሉ ወደ አንተ እንዲመለስ እኔ እረዳሃለሁ” ብለው ለዳዊት እንዲነግሩለት መልክተኞች ላከ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከዚያም አበኔር ለዳዊት እንዲህ ሲሉ ለዳዊት እንዲነግሩት መልክተኞች ላከ፥ “ምድሪቱ የማን ናት? ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እጄም ከአንተ ጋር ትሆናለች፥ እስራኤልንም ሁሉ ወደ አንተ እመልሰዋለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አበኔር በዚያን ጊዜ በኬብሮን ወደነበረው ወደ ዳዊት መልእክተኞች ልኮ “የዚህች ምድር ገዢ የሚሆን ማነው? እንግዲህ ከእኔ ጋር ስምምነት አድርግ፤ እኔም መላው እስራኤል በአንተ ቊጥጥር ሥር እንዲሆን ለማድረግ እረዳሃለሁ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አበ​ኔ​ርም ለዳ​ዊት፥ “ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርግ፤ እጄም ከአ​ንተ ጋር ትሆ​ና​ለች፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ወደ አንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ” ብለው በስሙ ይነ​ግ​ሩት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወዲ​ያ​ውኑ ላከ​ለት።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 3:12
15 交叉引用  

የይሁዳንም ሰዎች ሁሉ ልብ እንደ አንድ ሰው ልብ አድርጎ አዘነበለ፥ ወደ ንጉሡም ልከው፦ አንተ ከባሪያዎችህ ሁሉ ጋር ተመለስ አሉት።


እነሆም፥ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሥ መጡ፥ ንጉሡንም፦ ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች ለምን ሰረቁህ? ንጉሡንም ቤተ ሰቡንም ከእርሱም ጋር የዳዊትን ሰዎች ሁሉ ዮርዳኖስን አሻገሩ? አሉት።


አንተ የሚጠሉህን ትወድዳለህ፦ የሚወድዱህንም ትጠላለህ። መሳፍንትህና ባሪያዎችህን እንዳታስብ ዛሬ ገልጠሃል፥ ዛሬ ሁላችን ሞተን ቢሆን ኖር አቤሴሎምም ድኖ ቢሆን ኖሮ ደስ ያሰኘህ እንደ ነበረ ዛሬ አያለሁ።


ኢያቡስቴም አበኔርን ይፈራው ነበርና አንዳች ይመልስለት ዘንድ አልቻለም።


ዳዊትም፦ ይሁን፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፥ ነገር ግን አንድ ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ፊቴን ለማየት በመጣህ ጊዜ፥ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ካላመጣህልኝ ፊቴን አታይም አለ።


አበኔርም ዳዊትን፦ ተነሥቼ ልሂድ፥ ከአንተ ጋርም ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፥ ነፍስህም እንደ ወደደች ሁሉን እንድትገዛ እስራኤልን ሁሉ ለጌታዬ ለንጉሥ ልሰብስብ አለው። ዳዊትም አበኔርን አሰናበተው፥ በደኅናም ሄደ።


አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቆይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፥ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ሆዱን መታው፥ ሞተም።


ንጉሡም ባሪያዎቹን፦ ዛሬ በእስራኤል ዘንድ መኮንንና ታላቅ ሰው እንደ ወደቀ አታውቁምን?


跟着我们:

广告


广告