Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 24:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በዚያም ዳዊት ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ የሚቃጠልና የደኅነትንም መሥዋዕት አቀረበ። እግዚአብሔርም ስለ አገሪቱ የተለመነውን ሰማ፥ መቅሠፍቱም ከእስራኤል ተከለከለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ። ከዚያም እግዚአብሔር ስለ ምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የመጣውም መቅሠፍት ቆመ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በዚያም ዳዊት ለጌታ መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት አቀረበ። ከዚያም ጌታ ለምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የመጣውም መቅሰፍት ቆመ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ለእግዚአብሔርም መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ አቀረበ፤ እግዚአብሔርም የዳዊትን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የወረደውም የቸነፈር መቅሠፍት ከዚህ በኋላ ቆመ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በዚ​ያም ዳዊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ። ሰሎ​ሞ​ንም በኋላ ዘመን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤ ያን​ጊዜ አነ​ስ​ተኛ ነበ​ርና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሀገ​ሪቱ የተ​ለ​መ​ነ​ውን ሰማ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ተከ​ለ​ከለ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 24:25
16 交叉引用  

እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፤ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።


እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሰዊያውን ሰራ፥ እንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሰዊያው በእንጨቱ ላይ አጋደመው።


ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ፥ ከንጽሕም እንስሳ ሁሉ ከንጹሐን ወፎችን ሁሉ ወሰደ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀርበ።


የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት በብንያም አገር በጼላ በአባቱ በቂስ መቃብር ቀበሩት፥ ንጉሡም ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ስለ አገሩ የተለመነውን ሰማ።


ዳዊትም ጋድን፦ እጅግ ተጨንቄአለሁ፥ ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ፥ በሰው እጅ ግን አልውደቅ አለው።


ንጉሡ ዳዊትም ሸመገለ፤ ዕድሜውም በዛ፤ ልብስም ደረቡለት፤ ነገር ግን አይሞቀውም ነበር።


መዓቴንም በአንቺ ላይ እጨርሳለሁ ቅንዓቴም ከአንቺ ይርቃል፥ እኔም ዝም እላለሁ ደግሞም አልቈጣም።


የሚቀርብ ሁሉ፥ ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚቀርብ፥ ይሞታል፤ በውኑ ሁላችን እንሞታለንን? ብለው ተናገሩት።


በነጋውም ሕዝቡ ማልደው ተነሡ፥ በዚያም መሠዊያ ሠሩ፥ የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕትንም አቀረቡ።


ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም፦ እግዚአብሔር ሰላም ብሎ ጠራው። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለአቢዔዝራውያን በምትሆነው በዖፍራ አለ።


ሳኦልም፦ የሚቃጠል መሥዋዕትና የደኅንነት መሥዋዕት አምጡልኝ አለ።


ሳኦልም ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ፥ ይኸውም ለእግዚአብሔር የሠራው መጀመሪያ መሠዊያ ነው።


ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፥ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።


ሳሙኤልም አንድ የሚጠባ የበግ ጠቦት ወስዶ ለእግዚአብሔር ፈጽሞ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው፥ ሳሙኤልም ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኽ፥ እግዚአብሔርም ሰማው።


跟着我们:

广告


广告