Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 24:24 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ንጉሡም ኦርናን፦ እንዲህ አይደለም፥ ነገር ግን በዋጋ ከአንተ እገዛለሁ፥ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለዋጋ አላቀርብም አለው። ዳዊትም አውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ንጉሡ ግን ኦርናን፣ “እንዲህ አይደረግም፤ ዋጋውን ላንተ መክፈል አለብኝ፤ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በዐምሳ ሰቅል ብር ገዛ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ንጉሡ ግን ኦርናን፥ “መክፈል ያለብኝን ዋጋ ላንተ ከፍዬ እንጂ እንዲሁማ አይሆንም፤ ለጌታም ለአምላኬ የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ንጉሥ ዳዊት ግን “ይህስ አይሆንም፤ ዋጋውን መክፈል አለብኝ፤ እኔ ምንም ዋጋ ያላወጣሁበትን ነገር ለአምላኬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጌ ማቅረብ አይገባኝም” አለው፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት አውድማውንና በሬዎቹን በኀምሳ ጥሬ ብር ገዛ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ንጉ​ሡም ኦር​ናን፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን በዋጋ ከአ​ንተ እገ​ዛ​ለሁ፤ ለአ​ም​ላ​ኬም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያለ ዋጋ አላ​ቀ​ር​ብም” አለው። ዳዊ​ትም አው​ድ​ማ​ው​ንና በሬ​ዎ​ቹን በአ​ምሳ ሰቅል ብር ገዛ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 24:24
8 交叉引用  

ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ አይደለም ጌታዬ ስማኝ። እርሻውን ሰጥቼሃለሁ በእርሱም ዳር ያለውን ዋሻ ሰጥቼሃለሁ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼሃለሁ፤ ሬሳህን ቅበር።


የአገሩ ሰዎችም ሲሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፦ ነገሬን ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ አንተም ከእኔ ዘንድ ውሰድ፥ ሬሳዬም፥ በዚይ እቀብራለሁ።


አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ።


ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፤ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን አነሣሣው።


ዳዊትም “ይህ የእግዚአብሔር ቤት ነው፤ ይህም ለእስራኤል ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነው መሠዊያ ነው፤” አለ።


ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።


跟着我们:

广告


广告