Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 24:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ኦርናም ሲመለከት ንጉሡና ባሪያዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፥ ኦርናም ወጥቶ በንጉሡ ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፋ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ኦርናም ቀና ብሎ ንጉሡና ሰዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ከዚያም ወጥቶ ወደ መሬት ለጥ ብሎ ለንጉሡ እጅ ነሣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ኦርናም ቁልቁል ሲመለከት፥ ንጉሡና አገልጋዮቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ኦርናም ወጥቶ በንጉሡ ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፋ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ኦርናም ወደ ታች ሲመለከት ንጉሥ ዳዊትና ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ እርሱም በዳዊት ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ኦር​ናም ሲመ​ለ​ከት ንጉ​ሡና ብላ​ቴ​ና​ዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ኦር​ናም ወጥቶ በን​ጉሡ ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ሰገደ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 24:20
7 交叉引用  

ዓይኑንም አነሣና እነሆ ሦስት ስዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ እንዲህም አለ፥


በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሳኦል ሰፈር አንድ ሰው ልብሱን ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ መጣ፥ ወደ ዳዊትም በመጣ ጊዜ በግምባሩ ተደፍቶ እጅ ነሣ።


ዳዊትም እግዚአብሔር እንዳዘዘው እንደ ጋድ ነገር ወጣ።


ኦርናም፦ ጌታዬን ንጉሡን ወደ ባሪያው ያመጣው ምክንያት ምንድር ነው? አለ። ዳዊትም፦ መቅሠፍቱ ከሕዝቡ ላይ ይከለከል ዘንድ አውድማውን ከአንተ ገዝቼ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ልሠራ ነው አለው።


እርሱም፦ የሞተ ውሻ ወደምመስል ወደ እኔ የተመለከትህ እኔ ባሪያህ ምንድር ነኝ? ብሎ እጅ ነሣ።


በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት “እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን?” አለችው።


跟着我们:

广告


广告