2 ሳሙኤል 24:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ንጉሡም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን የሠራዊት አለቆች፦ የሕዝቡን ድምር አውቅ ዘንድ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ተመላለሱ፥ ሕዝቡንም ቍጠሩአቸው አላቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ስለዚህም ንጉሡ ኢዮአብንና ዐብረውት ያሉትን የጦር አዛዦች፣ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወዳሉት የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፤ ብዛታቸው ምን ያህል እንደ ሆነ ለማወቅ እንድችልም ተዋጊዎቹን መዝግቡ” አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ስለዚህም ንጉሡ ኢዮአብንና አብረውት የነበሩትን የጦር አዛዦች፥ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወዳሉት የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፤ ምን ያኽል ሕዝብ እንዳለ ማወቅ ስለምፈልግ ሕዝቡን ቁጠሩ።” አላቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ስለዚህም ዳዊት የጦሩ አዛዥ የሆነውን ኢዮአብን “የጦር መኰንኖችህን በማስከተል ከአገሪቱ ዳር እስከ ዳር ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወዳሉት የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ሄደህ ሕዝቡን ቊጠር፤ ምን ያኽል ሕዝብ እንዳለ ማወቅ እፈልጋለሁ” ሲል አዘዘው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ንጉሡም ከእርሱ ጋር የነበረውን የሠራዊት አለቃ ኢዮአብን፥ “የሕዝቡን ድምር አውቅ ዘንድ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሂድ፤ ሕዝቡንም ቍጠራቸው” አለው። 参见章节 |