Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 23:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የዳዊትም የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። ከፍ ከፍ የተደረገው፥ በያዕቆብም አምላክ የተቀባው፥ በእስራኤል ዘንድ መልካም ባለ ቅኔ የሆነ፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት ንግግር፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው፤ “በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣ ልዑል ከፍ ከፍ ያደረገው ሰው፣ የእስራኤል ተወዳጁ ዘማሪ፣ የእሴይ ልጅ የዳዊት የትንቢት ቃል ይህ ነው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። ከፍ ከፍ የተደረገው፥ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፥ የእስራኤል ተወዳጁ ዘማሪ የሆነው፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት የትንቢት ቃል ይህ ነው፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፥ በእስራኤልም ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የዳ​ዊ​ትም የመ​ጨ​ረሻ ቃሉ ይህ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ገው፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ የቀ​ባው፥ የታ​ማኙ ሰው፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ መል​ካም ባለ​መ​ዝ​ሙር የሆ​ነው፥ የታ​ማኙ የእ​ሴይ ልጅ የዳ​ዊት ንግ​ግር ይህ ነው፤

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 23:1
25 交叉引用  

ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ በኍለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብስቡ።


እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያረታ፥ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።


የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፥ ቸርነቱንም ለቀባው፥ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘላለም ይሰጣል።


በዚያም ቀን ዳዊት በአሳፍና በወንድሞቹ እጅ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ አስቀድሞ ትእዛዝን ሰጠ።


ተቀኙለት፤ ዘምሩለት፤ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።


በመሰንቆም ድምፅ ለምትንጫጩ፥ እንደ ዳዊትም የዜማን ዕቃ ለምታዘጋጁ፥


ዳዊትም ራሱ በመዝሙራት መጽሐፍ፦ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ይላል።


እርሱም፦ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው።


የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ሳይሞት የእስራኤልን ልጆች የባረከባት በረከት ይህች ናት።


የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤


ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር።


ዳዊትም የዚያ የኤፍራታዊው ሰው ልጅ ነበረ፥ ያም ሰው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ስሙም እሴይ ነበረ፥ ስምንትም ልጆች ነበሩት፥ በሳኦልም ዘመን በዕድሜ አርጅቶ ሸምግሎም ነበር።


ሴቶችም፦ ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም እልፍ ገደለ እያሉ እየተቀባበሉ ይዘፍኑ ነበር።


ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፥ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፥ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።


跟着我们:

广告


广告