Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 21:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ንጉሡም በሳኦል ልጅ በዮናታንና በዳዊት መካከል ስለ ነበረው ስለ እግዚአብሔር መሐላ የሳኦልን ልጅ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን አዳነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በእግዚአብሔር ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፣ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን ከሞት አተረፈ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በጌታ ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፥ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን ከሞት አተረፈ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ነገር ግን ዳዊትና ዮናታን እርስ በርሳቸው በገቡት የተቀደሰ ቃል ኪዳን ምክንያት ዳዊት የሳኦልን የልጅ ልጅ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን አሳልፎ አልሰጣቸውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ንጉ​ሡም በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል፥ በዳ​ዊ​ትና በሳ​ኦል ልጅ በዮ​ና​ታን መካ​ከል ስለ ነበ​ረው ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሐላ የሳ​ኦ​ልን ልጅ የዮ​ና​ታ​ንን ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴን ራራ​ለት።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 21:7
16 交叉引用  

ንጉሡም ሲባን፦ እነሆ፥ ለሜምፊቦስቴ የነበረው ሁሉ ለአንተ ይሁን አለው። ሲባም፦ እጅ እነሣለሁ፥ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስ ላግኝ አለ።


ንጉሡም ሊቀበለው ከኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፦ ሜምፊቦስቴ ሆይ፥ ከእኔ ጋር ስለ ምን አልወጣህም? አለው።


ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፥ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፥ ፈጥናም ስትሸሽ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፊቦስቴ ነበረ።


ዳዊትም፦ ስለ ዮናታን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት አንድ ሰው ቀርቶአልን? አለ።


አንተና ልጆችህ ሎሌዎችህም ምድሩን እረሱለት፥ ለጌታህም ልጅ እንጀራ ይሆነው ዘንድ ፍሬውን አግባ፥ የጌታህ ልጅ ሜምፊቦስቴ ግን ሁልጊዜ ከገበታዬ ይበላል አለው። ለሲባም አሥራ አምስት ልጆችና ሀያ ባሪያዎች ነበሩት።


የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት መጣ፥ በግምባሩም ወድቆ እጅ ነሣ፥ ዳዊትም፦ ሜምፊቦስቴ ሆይ፥ አለ፥ እርሱም፦ እነሆኝ ባሪያህ አለ።


ዳዊትም፦ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሃለሁና አትፍራ፥ የአባትህንም የሳኦልን ምድር ሁሉ እመልስልሃለሁ፥ አንተም ሁልጊዜ ከገበታዬ እንጀራ ትበላለህ አለው።


እኔ፦ በእግዚአብሔር መሐላ ምክንያት የንጉሥን ትእዛዝ ጠብቅ እልሃለሁ።


ዮናታንም እንደ ነፍሱ ስለ ወደደው ከዳዊት ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።


ዮናታንም ዳዊትን አለው፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ምስክር ይሁን፥ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በዚህ ጊዜ አባቴን መርምሬ፥ እነሆ፥ በዳዊት ላይ መልካም ቢያስብ ልኬ እገልጥልሃለሁ፥


ደግሞም እግዚአብሔር የዳዊትን ጠላቶች ሁሉ እያንዳንዱ ከምድር ባጠፋቸው ጊዜ ለዘላለም ቸርነትህን ከቤቴ አታርቀው።


ዮናታንም ዳዊትን እንደ ነፍሱ ይወድድ ነበርና እንደ ገና ማለለት።


ዮናታንም ዳዊትን፦ በደኅና ሂድ፥ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል ለዘላለም እግዚአብሔር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፥ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።


እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከባሪያህ ጋር አድርገሃልና ለባሪያህ ቸርነት አድርግ፥ በደል ግን ቢገኝብኝ አንተ ግደለኝ፥ ለምን ወደ አባትህ ታደርሰኛለህ?


ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ፥ ዳዊትም በጥሻው ውስጥ ተቀመጠ፥ ዮናታንም ወደ ቤቱ ሄደ።


ዳዊትም ለሳኦል ማለለት፥ ሳኦልም ወደ ቤቱ ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ወደ አምባው ወጡ።


跟着我们:

广告


广告