Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 21:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ዳዊትም ሄደ፥ ሳኦልንም በጊልቦዓ በገደሉ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ከሰቀሉአቸው ስፍራ ከቤትሳን አደባባይ ከሰረቁት ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ወሰደ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሄዶ የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ወሰደ፤ የኢያቢስ ገዦች፣ ፍልስጥኤማውያን ሳኦልን በጊልቦዓ ከገደሉ በኋላ እነርሱን ከሰቀሉት ከቤትሳን አደባባይ በድብቅ ወስደዋቸው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ዳዊት ሄዶ፥ ሳኦልን በጊልቦዓ በገደሉ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ከሰቀሉአቸው ስፍራ ከቤት ሻን አደባባይ ከሰረቁት ከያቤሽ ገለዓድ ሰዎች የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ወሰደ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በገለዓድ ምድር ወደምትገኘው ወደ ያቤሽ ሕዝብ ሄዶ የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም አመጣ፤ የያቤሽ ሕዝብ ዐፅሙን ያገኙት ፍልስጥኤማውያን ሳኦልን በጊልቦዓ በገደሉበት ቀን ሬሳዎችን ከሰቀሉበት ከቤትሻን አደባባይ በመስረቅ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዳዊ​ትም ሄደ፤ ሳአ​ል​ንም በጌ​ላ​ቡሄ በገ​ደ​ሉት ጊዜ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ከሰ​ቀ​ሉ​አ​ቸው ስፍራ ከቤ​ት​ሳን አደ​ባ​ባይ ከሰ​ረ​ቁት ከኢ​ያ​ቤስ ገለ​ዓድ ሰዎች የሳ​ኦ​ልን አጥ​ን​ትና የል​ጁን የዮ​ና​ታ​ንን አጥ​ንት ወሰደ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 21:12
15 交叉引用  

እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፥ የሳኦል ጋሻ በዘይት እንዳልተቀባ፥ የኃያላን ጋሻ በዚያ ወድቆአልና ዝናብና ጠል አይውረድባችሁ፥ ቍርባንንም የሚያበቅል እርሻ አይሁንባችሁ።


ወሬኛውም ጕልማሳ አለ፦ በድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ መጣሁ፥ እነሆም፥ ሳኦል ጦሩን ተመርኩዞ ቆሞ ነበር፥ ሰረገሎችና ፈረሰኞችም ተከትለው ደረሱበት።


የይሁዳም ሰዎች መጥተው በይሁዳ ቤት ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን በዚያ ቀቡት።


የሳኦልም ቁባት የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ያደረገችውን ለዳዊት ነገሩት።


ከዚያም የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ይዞ መጣ፥ የተሰቀሉትንም ሰዎች አጥንት ሰበሰቡ።


ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ተወግተውም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወደቁ።


ጽኑዓን ሰዎች ሁሉ ተነሥተው የሳኦልን ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ወሰዱ፤ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በኢያቢስም ካለው ከትልቁ ዛፍ በታች አጥንቶቻቸውን ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።


በነጋውም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልንና ልጆቹን በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።


በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ ዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ዓይነዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ታዕናክና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ መጊዶና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ሦስቱ ኮረብቶች ለምናሴ ነበሩ።


ፍልስጥኤማውያንም ተሰብስበው መጡ በሱነምም ሰፈሩ፥ ሳኦልም እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፥ በጊልቦዓም ሰፈሩ።


ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፥ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ ተወግተውም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወደቁ።


ሰልፍም በሳኦል ላይ ጠነከረ፥ ቀስተኞችም አገኙት፥ እርሱም ከቀስተኞቹ የተነሣ እጅግ ተጨነቀ።


ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፦ እነዚህ ቆላፋን መጥተው እንዳይወጉኝና እንዳይሳለቁብኝ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበርና እንቢ አለ። ሳኦልም ሰይፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።


跟着我们:

广告


广告