Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 21:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በዳዊትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል ቀጥሎ ቀጥሎ ራብ ሆነ፥ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ፊት ጠየቀ። እግዚአብሔርም፦ የገባዖንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳኦልና በቤቱ ላይ ደም አለበት አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዳዊት ዘመነ መንግሥት፣ በተከታታይ ለሦስት ዓመት ራብ ሆነ፤ ስለዚህ ዳዊት እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፣ “ሳኦል ገባዖናውያንን ስለ ገደለ፣ እርሱና ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዳዊት ዘመነ መንግሥት፥ በተከታታይ ለሦስት ዓመት ራብ ሆነ፤ ስለዚህ ዳዊት ጌታን ጠየቀ፤ ጌታም፥ “ሳኦል ገባዖናውያንን ስለ ገደለ፥ እርሱና ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በዳዊት ዘመነ መንግሥት ሦስት ዓመት ሙሉ ጽኑ ራብ ነበር፤ ዳዊትም ስለዚህ ጉዳይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጠየቀ ጊዜ እግዚአብሔር “ሳኦልና ቤተሰቡ ግድያ በመፈጸም በደል ሠርተዋል፤ ሳኦልም የገባዖንን ሰዎች ፈጅቶአል” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በዳ​ዊ​ትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል በተ​ከ​ታ​ታይ ራብ ሆነ፤ ዳዊ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠየቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “የገ​ባ​ዖ​ንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳ​ኦ​ልና በቤቱ ላይ ደም አለ​በት፥”

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 21:1
34 交叉引用  

በምድርም ራብ ሆነ አብራንምም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፥ በምድር ራብ ጸንቶ ነበርና።


በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ላይ ራብ ሆነ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወድ አቢሜሌክ ወደ ግውራራ ሄደ።


አገሮችም ሁሉ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወደ ዮሴፍ መጡ በምድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበርና።


የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡቱ ጋር ገቡ በከነዓን አገር ራብ ነበረና።


ራብም በምድር ጸና።


በፋንታው ነግሠሃልና እግዚአብሔር የሳኦልን ቤት ደም ሁሉ መለሰብህ፥ እግዚአብሔርም መንግሥትን ለልጅህ ለአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቶታል፥ እነሆም፥ አንተ የደም ሰው ነህና በመከራ ተይዘሃል አለ።


የኢያዕር ሰውም ዒራስ ለዳዊት አማካሪ ነበረ።


ንጉሡንም፦ እኛን ካጠፋ፥ ከእስራኤል ዳርቻ ሁሉ እንዳንቀመጥ መፍረሳችንን


ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ዳዊትም፦ ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር ብሎ በላያቸው አስነሣው።


ዳዊትም፦ ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ፍልስጥኤማውያንን በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ አለው።


ዳዊትም እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እርሱም፦ በኋላቸው ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ አትውጣ።


በገለዓድ ቴስቢ የነበረው ቴስብያዊው ኤልያስ አክዓብን “በፊቱ የቆምሁት የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ጠልና ዝናብ አይሆንም፤” አለው።


ኤልያስም ለአክዓብ ይገለጥ ዘንድ ሄደ፤ በሰማርያም ራብ ጸንቶ ነበር።


በሰማርያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነሆም፥ የአህያ ራስ በአምሳ ብር፥ የርግብም ኩስ የጎሞር ስምንተኛ የሚሆን በአምስት ብር እስኪሸጥ ድረስ ከበቡአት።


ኤልሳዕም ልጅዋን ያስነሥላትን ሴት “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነሥተሽ ሂጂ፤ በምታገኚውም ስፍራ ተቀመጪ፤ እግዚአብሔር ራብ ጠርቶአል፤ ሰባት ዓመትም በምድር ላይ ይመጣል፤” ብሎ ተናገራት።


እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ አትፍረድብኝ፥ የምትከራከረኝ ለምን እንደ ሆነ ንገረኝ።


የእህላችሁንም ድጋፍ በሰበርሁ ጊዜ፥ አሥር ሴቶች እንጀራቸውን በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፥ በሚዛንም መዝነው እንጀራችሁን ይመልሱላችኋል፤ በበላችሁም ጊዜ አትጠግቡም።


በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።


የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር በደሉ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፥ የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።


ስለ ማልንላቸው መሓላ ቁጣ እንዳይወርድብን ይህን እናድርግባቸው፥ በሕይወትም እንተዋቸው አሉአቸው።


እንዲህም ሆነ፤ መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ ከቤተ ልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።


ከእግዚአብሔርም፦ ገና ወደዚህ የሚመጣ ሰው አለን? ብለው ደግሞ ጠየቁት እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ በዕቃ መካከል ተሸሽጎአል ብሎ መለሰ።


የቅዒላ ሰዎች በእጁ አሳልፈው ይሰጡኛልን? ባሪያህስ እንደ ሰማ ሳኦል በውኑ ይወርዳልን? የእስራኤል አምላክ አቤቱ፥ እንድትነግረኝ እለምንሃለሁ አለ። እግዚአብሔርም፦ ይወርዳል አለ።


ዳዊትም፦ ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያን ልምታን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ሂድ፥ ፍልስጥኤማውያንን ምታ ቅዒላንም አድን አለው።


ዳዊትም ደግሞ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም መልሶ፦ ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁና ተነሥተህ ወደ ቅዒላ ውረድ አለው።


跟着我们:

广告


广告