Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 20:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ዳዊትም አቢሳን፦ አሁን ከአቤሴሎም ይልቅ የሚጎዳን የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ ነው፥ እርሱ የተመሸጉትን ከተሞች አግኝቶ ከዓይናችን እንዳያመልጥ፥ አንተ የጌታህን ባሪያዎች ወስደህ አሳድደው አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ዳዊትም አቢሳን፣ “ከአቤሴሎም ይልቅ አሁን የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ የበለጠ ጕዳት ሊያደርስብን ስለ ሆነ የጌታህን ሰዎች ይዘህ አሳድደው፤ አለዚያ የተመሸገ ከተማ አግኝቶ ያመልጠናል” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ዳዊትም አቢሳን፥ “ከአቤሴሎም ይልቅ አሁን የቢክሪ ልጅ ሼባዕ የበለጠ ጉዳት ሊያደርስብን ስለሆነ የጌታህን አገልጋዮች ይዘህ አሳደው፤ ያለዚያ የተመሸገ ከተማ አግኝቶ ያመልጠናል” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህ ንጉሡ አቢሳን “ሼባዕ ከአቤሴሎም ይበልጥ የከፋ ችግር ይፈጥርብናል፤ ወታደሮቼን ይዘህ ተከታተለው፤ አለበለዚያ የተመሸጉ ከተሞቼን ይዞ ከእኛ እጅ ሊያመልጥ ይችላል” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “አሁን አቤ​ሴ​ሎም ከአ​ደ​ረ​ገ​ብን ይልቅ የከፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ብን የቢ​ኮሪ ልጅ ሳቡሄ ነው፤ እርሱ የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች አግ​ኝቶ ከዐ​ይ​ና​ችን እን​ዳ​ይ​ሰ​ወር፥ አንተ የጌ​ታ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ወስ​ደህ አሳ​ድ​ደው” አለው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 20:6
17 交叉引用  

የአሞንም ልጆች ሶርያውያን እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ከአቢሳ ፊት ሸሹ፥ ወደ ከተማይቱም ገቡ፥ ኢዮአብም ከአሞን ልጆች ዘንድ ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።


ኦርዮም ዳዊትን፦ ታቦቱና እስራኤል ይሁዳም በጎጆ ተቀምጠዋል፥ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ባሪያዎች በሰፊ ሜዳ ሰፍረዋል እኔ ልበላና ልጠጣ ወይስ ከሚስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄዳላሁን? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም አለው።


ሰውዮውም ኢዮአብን፦ እኛ ስንሰማ ንጉሡ አንተንና አቢሳን ኢታይንም፦ ብላቴናውን አቤሴሎምን ማንም እንዳይነካው ተጠንቀቁ ብሎ አዝዞአልና ሺህ ብር በእጄ ላይ ብትመዝን እጄን በንጉሡ ልጅ ላይ ባልዘረጋሁም ነበር አለው።


ዳዊትም ሕዝቡን ከኢዮአብ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከኢዮአብም ወንድም ከጽሩያ ልጅ ከአቢሳ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከጌት ሰውም ከኢታይ እጅ በታች ሢሶውን ሰደደ። ንጉሡም ሕዝቡን፦ እኔ ደግሞ ከእናንተ ጋር እወጣለሁ አላቸው።


አሁን እንግዲህ ተነሥተህ ውጣ፥ ለባሪያዎችህም የሚያጽናናቸውን ነገር ተናገራቸው፥ ያልወጣህ እንደ ሆነ ግን አንድ ሰው ከአንተ ጋር በዚህች ሌሊት እንዳይቀር በእግዚአብሔር እምላለሁ፥ ይህም ከብላቴናነትህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ካገኘህ ክፉ ነገር ሁሉ ይልቅ ታላቅ መከራ ይሆንብሃል።


በዚያም ሦስቱ የጽሩያ ልጆች ኢዮአብና አቢሳ አሣሄልም ነበሩ፥ አሣሄልም እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበረ።


የጽሩያም ልጅ አቢሳ አዳነው፥ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፦ አንተ የእስራኤልን መብራት እንዳታጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም ብለው ማሉለት።


የጽሩያም ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሠላሳው አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን በሦስቱ መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፥ ስሙም እንደ ሦስቱ ተጠርቶ ነበር።


ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም በሰልፍ በገባዖን ወንድማቸውን አሣሄልን ገድሎ ነበርና አበኔርን ገደሉት።


እኔም ዛሬ ምንም ለመንገሥ የተቀባሁ ብሆን ደካማ ነኝ፥ እነዚህም ሰዎች የጽሩያም ልጆች በርትተውብኛል፥ እግዚአብሔር ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት አላቸው።


ንጉሡም አላቸው “የጌታችሁን ባሪያዎች ይዛችሁ ሂዱ፤ ልጄንም ሰሎሞንን በበቅሎዬ ላይ አስቀምጡት፤ ወደ ግዮንም አውርዱት፤


የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ጦሩንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፤ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ።


ደግሞ የጽሩያ ልጅ አቢሳ ከኤዶማውያን በጨው ሸለቆ ውስጥ ዐሥራ ስምንት ሽህ ሰዎች ገደለ።


ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።።


መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤


ዳዊትም ኬጢያዊውን አቢሜሌክንና የጽሩያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፦ ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚወርድ ማን ነው? ብሎ ጠየቃቸው፥ አቢሳም፦ እኔ ከአንተ ጋር እወርዳለሁ አለ።


跟着我们:

广告


广告