Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 20:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከዳዊት ተለይተው የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ተከተሉ፥ የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ ጀምረው ኢየሩሳሌም እስኪደርሱ ንጉሣቸውን ተከተሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ስለዚህ የእስራኤል ሰው ሁሉ ዳዊትን ከድቶ የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ተከተለ። የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንሥቶ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ከንጉሣቸው ሳይለዩ ዐብረውት ሄዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ስለዚህ የእስራኤል ሰው ሁሉ ዳዊትን ከድቶ የቢክሪን ልጅ ሼባዕን ተከተለ። የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንሥቶ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ከንጉሣቸው ሳይለዩ አብረውት ሄዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ስለዚህም እስራኤላውያን ዳዊትን ከድተው ከሼባዕ ጋር ሄዱ፤ የይሁዳ ሕዝብ ግን ታማኝነታቸውን በማጽናት ከዮርዳኖስ እስከ ኢየሩሳሌም ዳዊትን ተከትለው ሄዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከዳ​ዊት ተለ​ይ​ተው የቢ​ኮሪ ልጅ ሳቡ​ሄን ተከ​ት​ለው ሄዱ፤ የይ​ሁዳ ሰዎች ግን ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀም​ረው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስ​ኪ​ደ​ርሱ ንጉ​ሣ​ቸ​ውን ተከ​ተሉ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 20:2
12 交叉引用  

ንጉሡም ተመልሶ እስከ ዮርዳኖስ ድረስ መጣ። የይሁዳ ሰዎች ንጉሡን ሊቀበሉ ንጉሡንም ዮርዳኖስን ሊያሻግሩ ወደ ጌልገላ መጡ።


እንዲህም ሆነ፥ አንድ ብንያማዊ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሳቤዔ የሚባል ምናምንቴ ሰው ነበረ፥ እርሱም፦ ከዳዊት ዘንድ እድል ፈንታ የለንም፥ ከእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ ብሎ ቀንደ መለከት ነፋ።


ነገሩ እንዲህ አይደለም፥ ከተራራማው ከኤፍሬም አገር የሚሆን የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ የሚባል አንድ ሰው ግን በንጉሡ በዳዊት ላይ እጁን አነሣ፥ እርሱን ብቻውን ስጡኝ፥ እኔም ከከተማይቱ እርቃለሁ አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፦ እነሆ፥ ራሱ ከቅጥር ላይ ይጣልልሃል አለችው።


ዳዊትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ቤቱ መጣ፥ ንጉሡም ቤቱን ሊጠብቁ የተዋቸውን አሥሩን ቁባቶች ወስዶ ለጠባቂ ሰጣቸው፥ ቀለብም ሰጣቸው፥ ነገር ግን ወደ እነርሱ አልገባም፥ በቤት ተዘግተው እስኪሞቱም ድረስ ባልቴቶች ሆነው ተቀመጡ።


እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም እንደ ተመለሰ በሰሙ ጊዜ ልከው ወደ ሸንጎአቸው ጠሩት፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ አነገሡት። ከብቻው ከይሁዳ ነገድ በቀር የዳዊትን ቤት የተከተለ አንድ ሰው አልነበረም።


በይሁዳ ከተሞች በተቀመጡት በእስራኤል ልጆች ላይ ግን ሮብዓም ነገሠባቸው።


እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ጸጋ ባየ ጊዜ ደስ አለው፥ ሁሉንም በልባቸው ፈቃድ በጌታ ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው፤


跟着我们:

广告


广告